
የማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ የተለያየ ድጋፎች ተደረገለት።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚንስቴር እና አጋሮች ያገኛቸውን የኤሌክትሮኒክስ እና የናሙና ማመላለሻ ቁሳቁሶች ድጋፍ፣ ለክልል ላቦራቶሪዎች አድርጓል።
በርክክቡ ወቅት፣ የጤና ሚንስቴር ዲኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ጀነራል ዳይሬክተር ዶክተር ሳሮ አብደላ፣ የማዕ/ኢት/ክልል ህብ/ጤ/ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እና ሌሎች የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች እና የኢንስቲትዩት ኃላፊዎች እንዲሁም የክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ድጋፉ እንደ አገር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለውን አጠቃላይ የላቦራቶሪ ሥርዓት ግንባታ ለማጠናከር ከፍተኛ እገዛ ስለሚያደርግ ስለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና አጋር አካለትን አመስግነው ወደ ፊትም ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል።



