Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ህብረተሰቡ ጥራት ያለው ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ በግል የጤና ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ተግተው መስራት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።

መጋቢት 26/2017 (ወልቂጤ)

ህብረተሰቡ ጥራት ያለው ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ በግል የጤና ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ተግተው መስራት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ዋና ስራ ሂደት በግል የጤና ዘርፍ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።

የውይይት መድረኩን በንግግር የየከፈተቱት የመምሪያው ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በመንግስት የማይሸፈኑ አገልግሎቶች ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ በግል የጤና ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ተሳትፏቸውን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ህብረተሰቡ ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ የግል ተቋማት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው በዞኑ እስከ 150 የግል እና 62 የመንግስት የጤና ተቋማት ይገኛሉ።

ይህ ደግሞ በመንግሥት የማይሸፈኑ አገልግሎቶች በግል የጤና ተቋማት እየተሸፈኑ መሆናቸው ተናግረዋል።

በመሆኑም ተቋማቱ ያሳተፈ ቀልጣፋና ጥራት ያለው ፍትሀዊ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል የጋራ የውይይት መድረኮች የላቀ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ብለዋል።

በዚህም የእናቶች እና ህፃናት ጤና ማሻሻል፣ ተላላፊ በሽታዎች መከላከል እና ሌሎች የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

በመድረኩ የመወያያ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተጠቁሟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *