
የባህላዊ እና ዘመናዊ መድሀኒት ምርምር እና ልማት ስራዎች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የባህላዊ እና ዘመናዊ መድሀኒት ምርምር ልማት ዳይሬክቶሬት ስር የሚገኙ የደህንንት እና ፍቱንነት ምርምር እና ልማት ዲቪዢን ፤የባህላዊ ልማት ኒትሪውስቲካል ምርምር እና ልማት ዲቪዥን፤የመድሀኒት ቅመማ እና ጥራት ቁጥጥር ልማት ዲቪዢን እና ዘመናዊ መድሀኒት እና የሲልኮ መደሀኒት ምርምር እና ልማት ዲቪዢን የስራ ክፍሎች በዳይሬክቶሬቱ በዋነኝነት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እና በ ከፈተኛ አመራሮች ትኩረት የሚሹ እና እገዛ የሚፈልጉ ሁኔታዎችን በክፍሉ ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት ተካ ገለፃ የተደረገ ሲሆን የአህሪ ከፍተኛ አመራሮችና ስራ አስፈፃሚዎች ከ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በመገምገም ውይይት ተደርጓል፡፡
ሀገራችን ከምትፈልገው የሀገር ውስጥ የመድሀኒት ምርት ግብዓት ለመተካት እና ባህላዊ መድሀኒቶችን ወደ ምርት በመቀየር ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እና የጤና ቸግሮችን ለመፍታት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለመደግፍ እንዲሁም ያሉትን ክፈትቶች በመሙላት ወደ ግብ መድረስ የሚቻልበትን ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተካሄዷል፡፡
የባህላዊ እና ዘመናዊ መድሀኒት ምርምር ልማት ዳይሬክቶሬት ውስጥ እየተሰሩ ያሉ የመድሀኒቶች ምርምር እና የልማት ስራዎች ከፍተኛ አመራሩ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚያግዝ እና እንደሀገር የትኩረት አቅጣጫ መስክ እንደሆነ በመግለፅ እና ለተያዘው የባህላዊ መድሀኒት ምርትን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚደረገውን ርብርብ በጥናትና ምርምር ከመደገፍ አንጻር ሁሉም ተባብሮ በመስራት ትልቅ አስተዋጽኦ ማምጣት እንደሚቻል ተገልጻል፡፡



