Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ከየካቲት 14-17 2017 ዓ/ም በተካሄደው የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ወቅት ለተለዩ የቆልማማ እግር፣ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ

ከየካቲት 14-17 2017 ዓ/ም በተካሄደው የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ወቅት ለተለዩ የቆልማማ እግር፣ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የቀዶ ህክምና ዘመቻ በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በይፋ ተጀመረ፡፡

ከየካቲት 14-17 2017 ዓ/ም በተካሄደው የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ወቅት ለተለዩ የቆልማማ እግር፣ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ነፃ የቀዶ ህክምና ዘመቻ በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀመሯል፡፡

“የላቀ ብሔራዊ የመከላከል፣ ህክምናና አካታች ስርዓት ለአፈጣጠር ችግሮች” በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 24 እስከ 29 አለም አቀፍ ለአፈጣጠር ችግር ሳምንት /World Birth Defect Week / ነጻ የቀዶ ህክምናና በማህበረሰብ ውስጥ ግንዛቤ በመፍጠር እየተከበረ ይገኛል፡፡

በሆስፒታሉ የተጀመረው ነፃ የቀዶ ህክምና ዘመቻው በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን አፈጣጠር ችግር ሳምንትን ምክንያት በማድረግ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ዳዊት ዳንኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት በአፈጣጠር ችግሮች ምክንያት በማህበረሰቡ ውስጥ ተደብቀው ለማህበራዊና ለስነ ልቦናዊ ችግሮች የሚጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎችን በነጻ ቀዶ ህክምናና ቀድሞ መከላከል በሚቻልባቸው ዘዴዎች ዙሪያ ለዘርፉ ባለሙያዎች በቂ ግንዛቤ ለመስጠት የሚያስችል ዘመቻ መሆኑን ተናግረዋል።

ዘመቻው በክልል ደረጃ በተካሄደው የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ወቅት ለተለዩ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ፣ በተፈጥሮ ቆልማማ እግር የነጸ ቀዶ ህክምና መሆኑን ዶ/ር ዳዊት አብራርተዋል፡፡

የነጻ ቀዶ ህክምና ዘመቻው በክልሉ ለሁሉም መዋቅሮች በተደራሽ እንዲሆን የወራቤ፣ ንግስት ኢሌኒ እና ወልቂጤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች እንዲሁም ሀላባ አጠቃላይ ሆስፒታልና ግራር ቤት የታድሶ ማዕከል ህክምና ማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

የታካሚዎችና አስታማሚዎች ምግብ እንዲሁም የደርሶ-መልስ የትራንስፖርት ወጪ በአጋር ድርጅቶች የሚሸፈን እንደሆነም አንስተዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *