
ይህ የተገለጸው የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ማኔጅመንት የቢሮ የሰባት ወራት ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ ላይ ነው ፡፡
ቢሮው በሰባት ወራቱ የህብረተሰቡ ጤና የሚያሻሽሉ የበሽታ መከላከል ፣ ወረርሽኞችን የመቆጣጠር እና መደበኛ የጤና ስራዎችን ጨምሮ ተጨማሪ ደራሽ የጤና ስራዎች አፈጻጸም ገምግሟል ፡፡
የህክምና አገልግሎት ጥራት ፣ ሽፋን ፣ ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር ታይቷል ፡፡
በሰባት ወር የክልሉ ጤና ቢሮ አጠቃላይ የጤና ግብዓት አቅርቦት ስርጭት ስርዓት በማኔጅመንት አባላት ውይይት ተካሂዷል ፡፡
የጤና ተቋማት ግንባታ የተከናወኑ ተግባራት ያለበት ደረጃ በማኔጅመንት ተገምግሟል ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በመድረኩ ማጠቃለያ ቢሮው በሰባት ወር አፈጻጸም የተሻለ የፈጸሙ መዋቅሮች ተግባራትን ታች ወርዶ ማረጋገጥ ክፍተት ያለባቸው ደግሞ ልዩ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ኃላፊው ገልጸዋል ፡፡
ወረርሽኞችን መቆጣጠር ፣ ኤችአይቪ ኤድስ ላይ የግንዛቤ ፣ የቲቢ በሽታ ላይ እንዲሁም የምግብ እጥረት ያለባቸው ወገኖች ልየታ በቀጣይ በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ፡፡
የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ፣ የመአጤመ አባል ለማፍራት የተገኘውን ውጤት ህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲያገኝ መስራት ይገባል አስታውቀዋል ፡፡
በክልሉ ያሉ ሆስፒታሎች አሁን ካለው አገልግሎት አሰጣጥ በተሻለ እንዲያከናውኑ በቅርበት ድጋፍ እና ክትትል ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡
በቅርቡ በድምቀት የተካሄደውን ክልል አቀፍ የጤና ኤክስቴንሽን ንቅናቄ እስከ ቀበሌ በማድረስ አላማውን እንዲያሳካ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል ፡፡
በመድረኩ የቢሮው ምክትል ሀላፊዎች እና ማናጅመንት አባላት ስራዎችን በዳሬክተር ፣በዘርፍ እና እንደ ቢሮ በቅንጅት በቀሪ ወራት ለማሳካት እንደሚሰሩም አስተያየት በመስጠት ተጠናቋል ፡፡
በቢኒያም ገዙ



