
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በሚደገፉ 18 ወረዳዎች ለሚተገበረዉ ክትባት ያልጀመሩ /ዜሮ ዶዝ/ እና ክትባት ጀምረዉ ያቋረጡ ህፃናትን ለይቶ ለመከተብ የሚያስችል ዉይይት ከሚመለከቲቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ይገኛል
የክልሉ ጤና ቢሮ የሀላፊ አማካሪ አቶ አባይነህ ኤርቃሎ የእለቱን ፕሮግራም ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት እንደ ሀገር ከ3.9 ሚሊየን በላይ ህፃናት ክትባት ያልተከተቡ እና ክትባቱን ጀምረዉ ያቋረጡ መሆናቸውን ጠቅሰዉ እንደ ማዕ/ክል/ ደግሞ ከ185 ሺህ በላይ ህፃናት ክትባት ያልተከተቡ እና ክትባትን ጀምረዉ ያቋረጡ ህፃናት ስለመሆናቸዉ አመላክተዋል
የቢሮዉ የእናቶች እና ህፃናት ስርዓተ ምግብ አገ/ት ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሌጅሶ በፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት ክትባት ያልተከተቡና ክትባቱን ጀምረዉ ያቋረጡ ህፃናት ቁጥር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአለም በሦስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገልጸው ይህን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል
ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ከ20 ሺህ በላይ ክትባት ያልጀመሩ ህፃናትን ክትባት መከተብ ስለመቻሉ የጠቆሙት አቶ ተስፋዬ በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም የክትባት ተደራሽነት አጥረት በመኖሩ በተኩረት መስራት ይገባል።
አቶ ተስፋዬ አክለውም ጥራት ያለዉ የጤና አገ/ት ተደራሽ ከማድረግና ቴክኖሎጂን ከመጠቀም ባለፈ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል እና ጤናን ለማበልፀግ እንዲሁም ሞትን ለማስቀረት ህፃናትን በሙሉ ክትባት ማስከተብ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል ።
አጋር ድርጅቶች በተደጋጋሚ በበጀት ድጋፍ በማድረጋቸው ምስጋናቸውን ያቀረቡት ዳይሬክተሩ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።
በእለቱ በተለያዩ በዘርፉ አካላት የዉይይት መነሻ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል
በሸምሲያ አደም




