Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የክልሉን ህብረተሰብ ጤና ለመጠበቅ የሚያግዙ የጥናት እና ምርምር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ ፡፡

የክልሉን ህብረተሰብ ጤና ለመጠበቅ የሚያግዙ የጥናት እና ምርምር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ ያለውን የአእምሮ ጤና በሽታ ስርጭት ለማወቅ በሚያካሂደው ጥናት እና ምርምር ተሳታፊ መረጃ ሰብሳቢዎች ባለሙያዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ አዘጋጅቷል ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በክልሉ በአእምሮ ጤና በሽታ ላይ በጥናት እና ምርምር የተደገፈ መረጃ አለመኖሩ ለጥናቱ መካሄድ አንዱ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሌላው በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የአእምሮ ጤና በሽታ ከፍ ብሎ መታየቱን ሌላው እንደ መነሻ ምክንያት በመውሰድ የበሽታውን ስርጭት በግልጽ ለማወቅ በክልሉ በአስሩም ዞን እና ልዩ ወረዳዎች ጥናት ማድረግ እንደ ሚያስፈልግ በመታመኑ ነው ብለዋል ፡፡

ጥናት እና ምርምሩ መንግስት በበቂ መረጃ ላይ ተመስርቶ በአእምሮ ጤና በሽታ ላይ ምላሽ መስጠት እንዲችል እንዲሁም በክልሉ የበሽታ ስርጭት ደረጃ በማወቅ የጤና ተቋማት ዝግጁነትን ለማጠናከር እንደሚረዳ አቶ ማሙሽ ገልጸዋል ፡፡

በጥናቱ ተሳታፊ አካላት በአእምሮ ጤና ላይ በክልሉ መረጃ አለመኖሩን ተረድተው በሙያዊ ስነምግባር ጥራት ያለው ዳታ በመሰብሰብ እንዲሳተፉ አደራ ብለዋል ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጥናት እና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ስናፍቅሽ አየለ በበኩላቸው

የአእምሮ ጤና በሽታ ዙሪያ በክልሉ ጥናታዊ መረጃ አለመኖሩ ጠቅሰው በጥናት ላይ የተደገፈ መረጃ ለማግኘት የሚደረግ ነው ሲሉ ገልጸዋል ፡፡

ጥናት እና ምርምሩ በክልል ደረጃ ያለውን የአእምሮ ጤና በሽታ ስርጭትን ምን ያህል ስፋት እንዲለው ለማወቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለአዕምሮ ጤና በሽታ አስተዋጽኦ ያላቸው ምክንያቶችን መለየት ሌላው ከጥናቱ የሚጠበቅ ግኝት መሆኑንም ገልጸዋል ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሚካሄድ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል ፡፡

በቢኒያም ገዙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *