Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የፖሊዮ በሽታን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት አመራሩ እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

የካቲት 11/2017 የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻን አስመልክቶ ለከፍተኛ አመራሩ እና ለባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደዋል።

የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ምክትል ተጠሪ አቶ ረመቶ መሀመድ እንደገለጹት የፖሊዮ በሽታን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት አመራሩ እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ገልጸዋል።

የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በአለም እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ እና በዞኑ ደረጃ ለማጥፋት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አክለዋል።

የጤና መምሪያ የሃይማኖት አባቶች እና ባለድርሻ አካላት እና በየደረጃው ያሉ የአመራርና ባለሙያ የክትባት ዘመቻው ውጤታማ እንዲሆን የድርሻቸዉን እንዲወጣ አሳስበዋል።

ህጻናት በወቅቱ የሚሰጡ የፖሊዮ መከላከያ ክትባትን ካላገኙ ለአካል ጉዳተኝነት የሚዳርግ በሽታ በመሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሊያስከትቡ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አቶ ረመቶ መሀመድ አስተላልፈዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዳይሬክተር አቶ ለገሠ ጴጥሮስ በበኩላቸው በዘመቻው ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት በተቀናጀ መልኩ ክትባቱ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ሀገር አቀፍ የክትባት ዘመቻዎች እየተካሄዱ ውጤታማ ቢሆኑም ከጥራት አንጻር ጉድለቶች እንደሚስተዋሉ ተናግረው በአሁኑ የክትባት ዘመቻ የጥራት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ገልጸዋል።

ክትባቱ ውጤታማ እንዲሆን የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ትኩረት እንደሚሻ አሳስበዋል።

በዚህ መድረኩ ላይ የዞኑ አመራሮች፣ የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ማኔጅመንት አባላት፤ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *