Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ከየካቲት 14 እስከ 17/2017/ዓ.ም የሚካሄደው የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ለባለድርሻ አካላት የኦረንቴሽንና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረጉ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መሰለ ጫካ የፖለቲካና ሪዮት አለም ዘርፍ ሀላፊ አቶ መሠረት ሽፋ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አህመድ ኑሪ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታሪኩ ደምሴ እንዲሁም የዞን አመራሮች የወረዳ አስተዳዳሪዎች ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የጤና ፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን እና የፀጥታ መዋቅር አመራሮች ተገኝተዋል ።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጉግሳ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ከካቲት 14 እስከ 17/2017/ዓ.ም የሚደረገው የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በጥራትና በጥንቃቄ ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ የቅድመዝግጅት ስራ መሠራቱን ገልፀው በየደረጃ የሚገኘው አመራር ባለቤት ሆኖ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል ።

የፖሊዮ ዘመቻ . ክትባት እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት የሚሰጥ ሲሆን በተጨማሪ የፌስቱላና የማህፀን ውልቃት ችግር ያለባቸው መለየት፣ የስረዐተ-ምግብ ልየታ፣ ምንም ክትባት ያልተከተቡ ህፃናት መለየትና መከተብ እንዲሁም የቆልማማ እግር ችግር ያለባቸውና እና በተፈጥሮ የላንቃና የከንፈር መሰንጠቅ ችግር ያለባቸውን ህጻናት የመለየት ከክትባት ዘመቻ ስራው ጎን ለጎን እንደሚሰራ ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት እንዲሳተፍ አሳስብዋል ።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *