
በክልል አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የመጀመሪያ ዙር ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ውጤታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡
በክልል ደረጃ ለሚገኙ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ቡታጅራ ከተማ የአድቮኬሲ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንደተናገሩት በክልል አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የመጀመሪያ ዙር ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ውጤታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተለይ የሚዲያ ተቋማት ዘመቻውን በባለቤትነት ዕሳቤ በመምራት ለህዝብ ትክክለኛ መረጃና የአድቮኬሲ ሥራ በመከወን የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባም ኃላፊው አስገንዝበዋል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው በዘመቻው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ክትባቱን የሚወስዱ ሲሆን በጤና ባለሙያዎች ቤት ለቤት የሚሰጥ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡
የፖሊዮ ክትባት ስርጭት አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰው ለተሻለ ውጤታማነት በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ከዞንና፣ ከልዩ ወረዳ የጤና መምሪያና ፅ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት ከተገኙ አካላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ





