Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ከየካቲት 14-17/2017 ዓ.ም በዘመቻ የሚሰጠውን የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ እንዲሆን የክልሉ ጤና ቢሮ በትኩረት እየሰራ ነው የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ

የዘመቻውን ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዕቅድ ሰነድ እና የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ከመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ጎን ለጎን ተቀናጅተው የሚከናወኑ ተግባራት የቆልማማ እግር ልየታ፣ ምንም ክትባት ያልተከተቡ ህጻናት ልየታ፣ የምግብ እጥረት በሽታ ልየታ እና የማዐጤመ ስራዎች ያሉበት ደረጃ ላይ ተግባራትን በልዩ ትኩረት የመፈጸም ጉዳይ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጠይቀዋል።

የክትባት ጥራትና ደህንነት ማስጠበቂያ ፍሪጆች ጥገናና የተለያዩ የክትባት ግባዓት አቅርቦቶች የሚሳለጥበት ሁኔታዎች ላይ ቢሮው በትኩረት እየሰራ ስለመሆኑ የተናገሩት አቶ ሳሙኤል እስከ ታችኛው መዋቅር ያሉ ባለድርሻዎች ይህንኑ ተግባር ለማሳለጥ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የተቀናጀ የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ መከላከያ የቅድመ ዝግጅት እና እስከ መጨረሻው የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተመላክቷል።

የተቀናጀ የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አጠቃላይ ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች እና የማናጅመንት አካላት በተገኙበት ተደርጓል።

የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *