
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ክልላዊ የመረጃ ቅመራና ትንተና አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተደርጓል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ክልላዊ የመረጃ ቅመራና ትንተና ማዕከል መመ
ስረቱን ተከትሎ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት መደረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።
የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴንን ጨምሮ ከክልሉ ፓሊሲ ጥናትና ምርምር፣ ከወራቤ ዩኒቨርሲቲና ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከተውጣጡ አካላት ጋር የፓናል ውይይት ተደርጓል።
የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና የህብረተሰቡን የጤና አደጋዎች ቀድሞ በመተንበይ የቅድመ መከላከል ስራዎችን በማከናወን እንዲሁም ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ሲከሰቱ በፍጥነት በመቆጣጠር ተግባራትን በምርምር ስራዎች በማገዝ ጥራት ያለው የተናበበና ታዓማኒንቱ የተረጋገጠ የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን በማጠናከር መረጃን ለውሳኔ የመጠቀም ባህልን በማዳበር ረገድ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩቱ የመረጃ ቅመራና ትንተና ማዕከል መመስረቱ በክልሉ ላሉ ሁሉም የጤና ተቋማት የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን የተሳለጠ ያደርጋል ያሉት አቶ ማሙሽ በክልሉ ውስጥ ካሉ የዋቸሞ፣ የወራቤ፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የክልሉ ፖሊሲና ጥናት ምርምር እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተለያዩ የምርምር ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑም አስረድተዋል።
የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ በክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የተሰሩ የምርምር ስራዎች ውጤት አምጪ እንዲሆኑና የመረጃ አጠቃቀም ባህልን ለማሳደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ አደረጃጀት አጠቃቀምና ልውውጥ ስርዓቱን የማጎልበት የተጠኑ የምርምር ስራዎችን ተግባር ላይ እንዲውሉ የማድረግ ተግባራቶችን በልዩ ትኩረት መፈጸም ይገባልም ብለዋል።
እንደየተቋማቸው ተጨባጭ ሁኔታ የመረጃ ቅመራና ትንተና ስራዎችን እንዲሁም መረጃን ለውሳኔ የመጠቀም ባህልን የማሳደግና የምርምር ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑ የተናገሩት ፓናሊስቶቹ በቀጣይ ተግባራትን በልዩ ትኩረት ለመፈጸም ቁርጠኛ መሆናቸው ገልጸዋል።
የመረጃ ቅመራ ትንተና እና የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዌብሳይት መረጃ አጠቃቀም እንዲሁም በክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አጠቃላይ የተሰሩ የምርምር ስራዎች ላይ ያተኮሩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመጨረሻም ለIRB አባላት የእውቅና ስርተፊኬት የመስጠት መርሃ ግብር ተከናውኗል።
የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ





