Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል ከየካቲት 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ በሆሣዕና ከተማ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል።

በማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል ከየካቲት 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ በሆሣዕና ከተማ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል።

የከቲት 04/2017 ዓ.ም

የማዕከላዊ ኢ/ክ/ጤ/ቢሮ የህ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ፖሊዮ (nOPV2) ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ ከዞንና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ጤና ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ሥልጠና መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

በመሆኑም የመጀመሪያ ዙር ፖሊዮ (nOPV2) ክትባት ዘመቻ በሁሉም አከባቢዎች ዕድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ከየከቲት 14-17/ 2017 ዓ.ም በሰለጠነ ባለሙያ ቤት ለቤት በሚደረገዉ ዘመቻ ከዚህ በፊት ቢከተቡም ባይከተቡ በአፍ የሚሰጥ ክትባት እንደሆነ ተገልጿል።

የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ሥልጠናው በተመሣሣይ መልኩ በዞንና በልዩ ወረዳዎች ለሚመለከታቸው አካላት ከዘመቻዉ አስቀድሞ መሰጠት የሚጀምር ሲሆን ለክትባት ዘመቻው የሚያስልገው ግብአት እስከ ወረዳ ማዕከላት እንደሚሰራጭ ተገልጿል።

በስልጠናው መዝጊያ ፕሮግራም የተገኙት በክልሉ ህ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም ባለሙያዎች እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *