
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የድንገተኛ ጤና አደጋዎችን ቅኝትና ምላሽ ከማጠናከር አኳያ እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል በርካታ ተግባራቶች እየተከናወነ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ገልጿል።
በክልሉ ስር ከሚገኙ ዞንና ወረዳዎች ለተውጣጡ ድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ሰጪ ባለሙያዎች የሚሰጠው ስልጠና በዛሬው ዕለት በቡታጅራ ከተማ ተጀምሯል።
የማ/ኢት/ክ/ጤ/ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገስ ጴጥሮስ በመክፈቻ ንግግሩ እንደገለጹት ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የመልሶ ምልከታ ማድረጉ ወረርሽኙ በቀጣይ ጊዜ መልሶ እንዳይከሰት በማድረግ የማህበረሰቡን ጤና ከማስጠበቅ አኳያ ጉልህ ሚና እንዳልው ገልጸዋል ።
የመልሶ ምልከታ ስራው የኮሌራ ወረርሽኝ እንዲከሰት ምክኒያት የሆኑ ጉዳዮች እንዲሁም በወቅቱ ያጋጠሙ ችግሮችን ከማወቅ አንጻር በርካታ ለውጥ እያመጣ ያለ ቢሆንም ህብረተሰቡ የሚፈልገውን የጤና ፍላጎት ከማሟላት አኳያ ብዙ ስራዎች መስራት እንደሚጠበቅ የገለጹት አቶ ለገሰ ይህ ወርክ ሾፕ የሚያስገኛቸውን ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ታሳቢ ያደረገ ተግባርን አጠናክሮ ለማስቀጠል በየደረጃው ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ አመላክተዋል።
ስልጠናው በቀጣይ ቀናቶችም የሚቀጥል ይሆናል።
የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት



