Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ልማት ህብረት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ላይ ያላቸዉን ተሳትፎ የሚያጠና የጥናት ስራ በተመለከተ በዛሬ ዕላት ለመረጃ ሰብሰቢዎች በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊሲ ጥናት ምርምር በጋራ በመሆን ” Level of Women Development Union Engagement on Health Extension programm at Central Ethiopia Region” በማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል የሴቶች ልማት ህብረት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ላይ ያላቸዉን ተሳትፎ የሚያጠና የጥናት ስራ በተመለከተ በዛሬ ዕላት ለመረጃ ሰብሰቢዎች በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ። ይህ ጥናት ሲጠናቀቅ የሴቶች ህብረት አደረጃጀት በጤናው ዘርፍ ላይ ያላቸውን ሚና መለየት እና ቀጣይ የተሳትፎ እስትራቴጂ በመለየት ለክልሉ የጤና ስርዓት ተጠቃሚነት ላይ የጎላ አስተዋጽኦ ሊኖረው የሚችል ጥናት መሆኑን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የጥናት እና ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ዶ/ር ስናፍቅሽ አየለ በመድረኩ ላይ አንስተዋል ። በውይይቱ ዶ/ር ፈለቀችተ/ማሪያም ከክልሉ ፐሊሲ ጥናት ኢንስትቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተገኙ ሲሆን የስልጠናውን መድረክ የክልሉ ጤና ቢሮ ም/ሀላፊ እና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሸናፊ ፔጥሮስ በይፋ አስጀምረዋል ።

ምንጭ – የክልሉ ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *