
ከክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በአቶ ማሙሽ ሁሴን፣ ምክትል ኃላፊና የጤና ቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ አባይነህ ኤርቃሎን፣ ዳይሬክተሮችና ከፍተኛ ኤክስፔርቶቾ ጨምሮ የዞኑ የእስከአሁን ያለው የማዐጤመ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን በአፈጻጸም ግምገማ መነሻ ላይ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ደሣለኝ ሽጉጤ አጠቃላይ የዞኑን ነባራዊ ሁኔታ ከአፈጻጸሙ ጋር በስፋት አንስተዋል።
በመቀጠልም በቀረበዉ ሪፖርት መነሻ ከክልል ጤና ቢሮ አካላት ምንም እንኳ መምሪያው ወረዳዎችን ተከፋፍሎ እየደገፈ ቢሆንም ዞኑ ከሌሎች አቻ ዞኖች አንፃር ገና ሰፊ ሥራ የሚጠብቀው እንደሆነ አንሥተዋል። በተጨማሪም ሥራው በቅንጅት የሚመራ በመሆኑ ከዞን እስከ ቀበሌ ያለው አመራር የባለቤትነት ሥሜት ኖሮት መንቀሳቀስ እንደሚገባም ተጠቁሟል።
ከዚህም በመቀጠል ከክልልና ከዞኑ የተወጣጣ ቡድኑ በተለይም ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ ያሉ መዋቅሮችን ለመደገፍና በየወረዳው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለማየት በተቀመጠው የግዜ ገደብ ተግባሩ የሚፈጸምበትን አቅጣጫዎችንም ለማስቀመጥ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ላይ በጊቤና በምሻ ወረዳ በአቶ ማሙሽ ሁሴን የሚመሩት ቡድን፣ ሻሾጎ ወረዳንና ቦኖሻ ከተማ አስተዳዳን በአቶ ግርማ ወንድሙ የሚመራ ቡድን፣ እንዲሁም ሶሮና ምዕ/ሶሮን በአቶ አባይነህ ኤርቃሎ የሚመራ ቡድን የወረዳዎችንና የቀበሌያትን ነባራዊ ሁኔታ የየመዋቅሩ አስተባባሪ አካላት ባለበት መገምገም ተችሏል።
በመቀጠልም ቀሪ ወረዳዎችን በተለይም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያለባቸውን በመለየት እንደምደግፉ አንሥተው ዞኑ አሁን ካለበት ዝቅተኛ አፈጻጻም ማውጣት እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ ተቀሞጧል።

