Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የጤና ሚስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌይኒ ተርኪኺን የተመራ ልዑካን ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

Ministry Of Health

የጤና ሚስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌይኒ ተርኪኺን የተመራ ልዑካን ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

____________

የጤና ሚስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌይኒ ተርኪኺን የተመራ ልዑካን ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ራሺያ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸው ትብብር በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ ወዳጅ ሀገራት መሆናቸውን የገለጹት የጤና ሚኒስተር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በጤናው ዘርፍ ያለውን ትብብር አሁን ላይ ካለው የበለጠ ለማጠናከር የትብብር ስራዎች እንደሚያጎለብቱ ተናግረዋል፡፡

በተለይ በጤናው ዘርፍ ድንገተኛ የማህረሰብ ጤና አደጋዎችን ፈጣን ምላሽ በመስጠት፣ የህክምና ግበዓቶችና መድኃኒቶች በመደገፍ፣ የሀገር ውስጥ አመራቾችን አቅም በመፍጠር፣ እና ክትባቶች በሀገር ውስጥ ማምረት ስለሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪየ ከልዑካኑ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌይኒ ተርኪኺን በበኩላቸው የድንገተኛ የማህበረሰብ አደጋዎችን ምላሽ መስጠት እንዲቻል የትብብር ስራዎች እንደሚጠናከር አልፎም ስልጠናና ልምምድ ልውውጦች እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *