Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የጽዱ ጤና ተቋም ኢኒሺዬቲቭ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ::

Dr.Mekdes

በጤና ሚኒስቴር እየተተገበረ የሚገኘው እና የጽዱ ኢትዮጵያ አካል የሆነው የጽዱ ጤና ተቋም ኢኒሺዬቲቭ አፈጻጸም ግምገማ ታካሂዷል፡፡

ለጤናው ዘርፍ ጽዳት መሰረት መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በመድረኩ የገለጹ ሲሆን፤ ንጹህ ጤና ተቋም ኢኒሺዬቲቭ ከጤና ተቋም ባለፈ በቤተሰብ ደረጃ ንጹህ መጸዳጃ ቤትን መገንባትን ያካትታል ብለዋል፡፡ የውይይት መድረኩ በኢኒሽዬቲቩ ትግበራ የጤና ተቋማት ሊያሳኳቸው የሚገቡ ግቦችን በግልጽ ለማስቀመጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም አክለዋል፡፡

በመድረኩ በኢኒሺዬቲቩ ትግበራ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ መቻሉን የተናገሩት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፤ ኢኒሽዬቲቩ በ150 የጤና ተቋማት ትግበራው መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በሶስት ምእራፍ የሚካሄደው ፕሮጀክት፤ የጤና ተቋማት እድሳት፣ ግንባታ እና የማስዋብ ስራዎችን ያካትታል፡፡ የጤና ተቋማት የንጹህ ውሃ አቅርቦትን ማሻሻል እና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ መሰራት እንዳለበት በመድረኩ አቅጣጫ ተቀምጧል ሲል ሚኒስቴር መ/ቤቱ በፌስቡክ የማህበራዊ የትስስር ገጹ አጋርቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *