Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የጋራ ውይይት በየም ዞን ሳጃ ከተማ እያደረገ ይገኛል

የቢሮው ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በበኩላቸው የዕለቱ ግምገማ ትኩረት የሚያደርገው የመጀመሪያ ዙር ጂኤስሲ እና የ2017 ሩብ አመት አፈጻጸም ሆኖ የትኩረት አቅጣጫው መሆን ያለበት በፌደራል ደረጃ በተቀመጠው የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አሀድ እምርታ ማምጣት ነው ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠው ፈጣንና ዘላቂ የልማት ግብ የሚያጠነጥነው የእናቶች እና ህጻናት ተግባራት ላይ፣ የወባ ወረርሽኝ እና በሌሎች የጤና ጉዳዮች ላይ በመሆኑ ከዚህ መነሻ አስሩም መዋቅር በዚህ መሠረት ተግባራትን ሊያሳልጡ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የወባ በሽታ ወረርሽኝ በህብረተሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመቆጣጠር ህብረተሰቡን ያሳተፈ የንቅናቄ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

አስተዳዳሪው አክለውም በዞኑ የወባ ጫናን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ያደረጉት ርብርብ ለቀጣይ ለሚሰሩት ተግባር የስራ ተነሳሽነትን የፈጠረ አጋጣሚ መሆኑንም አስረድተዋል ።

የቢሮው 2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የድንገተኛ አደጋዎች ወቅታዊ ሁኔታ፣ በጤና ኤክ/ሽን ፕሮግራም ትግበራ ላይ የተሰራ የጥናት ውጤት፣ በጤና ተቋማት አገ/ት አሰጣጥ ላይ የተሰራ የዳሰሳ ጥናት ግኝት ሰነዶች ቀርበው ውይይት የሚደረግ ይሆናል።

የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *