Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ማሳላጫ ማዕከል መጎልበት በጤናው ሴክተር የማይንገራገጭ ስርዓት ለመገምባት ወሳኝ ነው አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ ኃላፊ

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ማሳላጫ ማዕከል መጎልበት በጤናው ሴክተር የማይንገራገጭ ስርዓት ለመገምባት ወሳኝ ነው አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ ኃላፊ

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ማሳላጫ ማዕከል ሳምንታዊ የአፈጻጸም ግምገማ ከዞንና ከልዩ ወረዳዎች ጋር በበይነ መረብ አካሂዷል።

በሳምንቱ 64,307 ሰዎች የወባ በሽታ ምርመራ ማድረጋቸውንና 21,158 ሰዎች የወባ በሽታ ተገኘቶባቸው ህክምና ማግኘታቸውን የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል።

ውይይቱን በበይነ መረብ የመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በጤና ተቋማት የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት መደበኛና ድንገተኛ የጤና አደጋዎችን አጣምሮ በመምራት የማይገራገጭ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ አሰጣጥ ማሳላጫ ማዕከል በመደበኛነት (ሳምንታዊ) ከመደበኛው የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ከዓቅም በላይ የሆኑ የጤና ጉዳዮች ሲኖሩ ተለይተው የምላሽ አሰጣጥ እቅድ በማዘጋጀት ተግባራዊነቱን ለማረጋገጥ አጋዥ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በአፈጻጸም ሂደት የሚሰተዋሉ ጉድለቶችን በማረም የድርጊት መርሃ- ግብር አስቀምጦ ምላሽ በመስጠት ተግራትን መፈጸም ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የተናገሩት ኃላፊው የወባ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን በመጥቀስ በተለይም በአካባቢ ቁጥጥርና በአጎበር አጠቃቀም ዙሪያ ማህበረሰቡን ያሳተፉ እና ቀጣይነት ያላቸው ስራዎችን ለማሳለጥ እየተደረገ ያለው ርብርብ የተለየ ስልትና ዘዴ ሊታከልበት ይገባል ብለዋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ ከወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ስራዎች ጋር በተያያዘ የክልሉ መንግስት የክልሉ ጤና ቢሮ የፊት አመራሮች በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እያደረጉ ያሉት ርብርብ የወባ በሽታ ጫናን በመቀነስ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስረድተዋል።

በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የወባ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት አቶ አሸናፊ ወቅታዊ መረጃዎችን በተዘጋጀላቸው የሪፖርት መላኪያ ፎርማት መሠረት በወቅቱ ለሚመለከተው አካል መላክ ይገባል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው የወባ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል በቅንጅት በተደረገው ርብርብ በክልሉ ከፍተኛ የወባ ጫና ከነበረባቸው 37 ወረዳዎች የ22ቱን ወረዳዎች መቀነስ መቻሉን ጠቁመው የወባ በሽታ ጫናን ትርጉም ባለው መልኩ ለመግታት የምላሽ እና የድጋፍ ስራዎችን በማጠናከር ተግባራትን በተናበበ መንገድ መፈጸም እንደሚገባ ተናግረዋል።

የወባ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አቶ ማሙሽ አክለው ገልጸዋል።

በቀረቡ ሰነዶች ላይ ኃሳብ እተያየት የተሰጠባቸው ሲሆን በየደረጃው የተቀመጡ እና ውሳኔ የተላለፈባቸው ተግባራትን ተፈፃሚነት ማረጋገጥ ፣በዘመቻ መልክ ተፈጻሚ እየተደረጉ የሚገኙ የተግባራን ተቀናጅቶ በመስራት፣ የምግብ እጥረት ክስተት ለአብዛኞቹ በሽታዎች መፈጠር ዜጎችን ለሌሎች በሽታዎች የመጋለጥ እና መዛመት ትልቁ አስተዋፅዖ የሚያበረክት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ችግሮችን መፍታት ፣መታረም የሚገባቸውን ጉዳዮችን ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተመላክቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *