በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ከ165 ሚሊየን በላይ ብር ወጪ የተደረገበት
የቂልጦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
በምረቃ ስነ ስርዓቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፣በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ሌሎች የክልል እና የስልጤ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የቂልጦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመንግስት እና በህዝብ ተሳትፎ ለምረቃ የበቃ ሲሆን ለግንባታው 100ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል።
የአካባቢው ህብረተሰብ እና ባለሀብቶች ለሆስፒታሉ የህክምና ቁሳቁሶች ግብአት 65 ሚሊየን ብር የገንዘብ ተሳትፎ አድርገዋል።
የሆስፒታሉ መገንባት የወረዳውን እና አጎራባች አካባቢዎች ህዝብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።
በተስፋዬ መኮንን