Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማህበረሰብ ግንዛቤ ስራዎችን በማጠናከር የወባ በሽታን መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ።

በወባ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀው የውይይት መድረክ በቡታጅራ ከተማ መካሄዱን የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ ገልጿል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘርሁን እሸቱ የወባ በሽታ የሚያስከትለዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ መገናኛ ብዙሃን በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

የወባ በሽታን ከመከላከል አኳያ መገናኛ ብዙሃን የተጫወቱት አይተኬ ሚና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ መሆኑን ያመላከቱት አቶ ዘሪሁን የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ቀመጠቀም ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ተግባራት መፈጸም እንደሚገባ ገልጸዋል።

በሽታውን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራት በጠንካራ የሚዲያ ሞኒተሪንግ እና የህዝብ አስተያየት መደገፍ አለበት ያሉት ኃላፊዉ የማህበረሰብ ንቃተ ጠናን የሚያሳድጉ ጉዳዮችን በልዩ ትኩረት ማከናወን ይገባል ብለዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በበኩላቸው የወባ በሽታ ስርጭት በበቀጣይ ሁለት ወራት ከአየር ንብረት ለውጡ ጋር ተያይዞ የመጨመር አዝማሚያ ሊያሳይ ስለሚችል የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የህብረተሰቡን ንቃተ ጤና የማሳደግ ስራዎችን በማጠናከር፣ ትክክለኛ መረጃ ከትክክለኛው የመረጃ ምንጭ የመቀባበል ስርዓቱን ማሳለጥ እንደሚገባ አቶ ሳሙኤል አክለዋል።

ሰማኒያ በመቶ የሚሆኑ የክልሉ አካባቢዎች ለወባ በሽታ ተጋላጭ መሆናቸውን ከቀረበው ሪፓርት መረዳት የታቸለ ሲሆን ከነዚህ አካባቢዎች 120 ቀበሌያት ተለይተው የተለያዩ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ሲሰራ መቆየቱ ተመላክቷል።

በክልሉ የተከሰተውን የወባ በሽታ ለመቆጣጠር የክልሉ መንግስት የሰጠው ትኩረት አበረታች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የክልሉ ጤና ቢሮ ለአንድ ወር በግብረ ኃይል እስከታችኛው መዋቅር ወርዶ የተጠናከረ መሰራቱንም የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል።

የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *