Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጥናት ለሚያደርግ የጥናት ቡድን ስምሪት መሰጠቱ ተገለጸ።

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ለጥናታዊ ቡድኑ የስራ ስምሪት በሰጡበት ወቅት ጥናቱ በክልሉ ባሉ ሁሉም መዋቅሮች በ39 ጤና ጣቢያዎች በ10 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች እና በ3 አጠቃላይ ሆስፒታሎች በጥናት የተደገፈ ተግባር የሚፈጽም መሆኑን አስረድተዋል።

የሰው ሀይል ውጤታማነት፣ የግብአት እና የመድሀኒት አቅርቦት እንዲሁም አስተዳደርን፣ የፋይናንስ ስርአት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እንዲሁም በጤና ተቋማት የሚታዪ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ትኩረት ባደረገ መልኩ ጥናት እንደሚደረግ አቶ ሳሙኤል አክለው ገልፀዋል።

የጥናት ግኝቱ የጤናው ሴክተር ላይ በተለይም የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት መሻሻል ላይ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሳሙኤል ለዚሁ ተግባር ስኬታማነት በየደረጃው ያሉ መዋቅሮች እና ጤና ተቋማት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ እና ትክክለኛ መረጃ ለጥናት ቡድኑ መስጠት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል:።

የክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ለጥናቱ በቢሮው በኩል በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልፀው የጥናት ቡድኑ የጥናቱን አላማ በተገቢው በመረዳት ተግባሩን በጥብቅ ስነምግባር ሊፈጽሙት እንደሚገባ አሳስበው

ጥናቱ በአራት ቡድን 52 ጤና ተቋማት ላይ ለቀጣይ 15 ቀናት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *