Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ሣምንታዊ የEOC ግምገማ አካሂዷል

የወባ በሽታ ስርጭትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር እንዲቻል ለማድረግ ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ማህበረሰቡ ድረስ የመከላከልና የቁጥጥር ሥራ ላይ በንቃት ማሳተፍ እንደሚገባ ተገልጿል።

የወባ በሽታ በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖና ጫና ለመከላከልና ለመቆጣጠር በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉት ርብርብ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተመላክቷል ።

የወባ መከላከል ተግባራትን ለማጠናከር በወረዳዎች የተሰራ በድጋፍና ክትትል የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ተወካይ አቶ ጁሀር አድማማ በቀጣይ በዋና የወባ ስርጭት ወቅት መተግበር ያለባቸውን ነጥቦች አስቀምጠዋል።

የወባ በሽታን ለመከላከል የምንሰራቸው ስራዎች ውጤታማነታቸውን በተገቢው በመፈተሽ የክረምቱን ዝናብ ተከትሎ ከፍተኛ ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል ታሳቢ ያደረገ ከምንግዜውም በላይ የመከላከልና የቁጥጥር ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ በትኩረት መሰራት ስለሚገባቸው ጉዳዮች አቶ ጁሀር ያብራሩ ሲሆን የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎችን ማህበረሰቡን በማሳተፍ በተደራጀ መልኩ መምራት፣ በወረዳና በከተማ አስተዳደር የወባ ጫና በከፍተኛ ደረጃ የሚስተዋልባቸውን ቀበሌያት በጎጥ በመለየት በልዩነት የምላሽ ስራ መስራት እንደሚገባ በመግለጽ RRT በማጠናከር ከመደበኛ ውይይት በተጨማሪ በየ3 ቀኑ የወባና ሌሎች በወረርሽኝ መልክ ሊነሱ የሚችሉ በሽታዎችን በመገምገም ለዞን ሪፖርት በየ3 ቀኑ መላክ ፣ አጎበር አጠቃቀም ላይ መሠረታዊ ጉድለት መኖሩን መነሻ በማድረግ አጎበር ለታለመለት አላማ ብቻ እንዲውል በማድረግ ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት የመምራት ስራ ተጠባቂ መሆኑን አስረድተዋል።

የጤና ኤ/ን ባለሙያዎች ቤት ለቤት ከማስተማሩና ማህበረሰቡን ከማሳተፍ ጎን ለጎን በጤና ኬላ ደረጃ ምርመራ እና ህክምና እንዲሰጡ ማድረግ ፣ በስራ ላይ የማይገኙ እና ተግባሩን የማይመሩ ጤና ኤ/ን ባለሙያዎች ተለይቶ ወደ ስራ ማስገባት ፣የሚመጣውን ውስን ግብዓት ለተጠቃሚ መድረስ አለመድረሱን ክትትል ማድረግ፣ ለህክምና አገ/ት የሚመጡ መድሃኒቶች በግል መድሃኒት መደብር እየተቸበቸበ ስለመሆኑ ክትትል ማድረግ እና የላቡራቶሪ አገልግሎት ጥራትን በተገቢው መፈተሽ ይገባልም ተብሏል ።

በመጨረሻም ጤና ተቋማትን ባለቤት እንዲሆኑና የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባሩን እንዲያግዙ ከማድረግ ባለፈ የመረጃ ጥራትን ማረጋገጥ፣ ሪፖርት ገምግመው እንዲልኩ እና የሪፖርት ቀሪ መረጃ እንዲያደራጁ ማድረግ ተገቢ መሆኑ ተገልጿል ።

ለስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ዘገባ

የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *