Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማ/ኢት/ክ/ሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል በሳምንታዊ እና ወቅታዊ የጤና ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል።

የወባ መከላከልና መቆጣጠር፣ የምግብ እጥረት፣ ፣የኩፍኝ እንዲሁም በሌሎች የጤና ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተከናወኑ ተግባራት ፣የጤና ተቋማት ለወባ ህክምና ዝግጁ በማድረግ ፣የቤት ለቤት ቅኝት፣አሰሳ እና የታመሙ ሰዎችን ቶሎ በማከም ረገድ መሻሻሎች መታየታቸውንና ከባለፈው ሳምንት በተወሰነ መልኩ የመቀነስ አዝማሚያ ማሳየቱን የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች የማስተባበሪያ ማዕከልና የቀውስ አስተዳደር ግብረ ሃይል የቅድመ ዝግጁነትና የምላሽ ስራዎችን በተገቢው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል ።

ህብረተሰቡን ያሳተፈ የወባ መከላከልና የመቆጣጠር ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል የወባ በሽታ የማህበረሰቡ የጤና ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አቶ አሸናፊ አክለው ገልጸዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን የስርዓተ ምግብ ልየታ አገልግሎት ማሻሻል፣ የግብዓት አጠቃቀምና ክትትል ስራን ማጠናከር በጤናው ሴክተር ቀጣይነት ያለው የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራን በማጎልበት ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር የወባ በሽታ ዳግም የማህበረሰቡ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ብርቱ ርብርብ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የወባ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ኢንስቲትዩቱ ከጤና ቢሮ ከተዋቀረ በማኔጅመንት አባላት የሚመራ የከፍተኛ ባለሙያዎች የድጋፍ ክትትል ቡድን እስከታችኛዉ መዋቅር ድረስ አሰማርቶ እየሰራ ያለው ስራ በቀጣይም እስከታችኛው መዋቅር ያሉ ባለድርሻ አካላት አጠናክረው ሊያስቀጥሉት እንደሚገባም ገልጸዋል ።

የወባ በሽታ ጫናን ለመቀነስ በየደረጃው እየተደረገ ያለው ርብርብ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ እና የወባ ጫና ከፍ ብሎ የሚታይባቸው የክልሉ አካባቢዎች የተጠናከር የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን መተግበር እንዳለባቸው ተመላክቷል።

የማ/ኢት/ክ/መ/ ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *