ጥቅምት_22_2017 በስልጤ ዞን ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ሙጎ ተራራ ቀበሌ ዲላ ቆቶ ተብሎ በሚጠራ አከባባቢ ትላንት ሌሊት 11:00 ሰዓት አከባቢ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ የመሬት መንሸራተት አደጋ መከሰቱ ተገልጿል።
በአደጋውም አንድ የመኖሪያ ቤት ጨምሮ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማስከተሉን ተገልጿል።
አደጋውን አስመልክቶ የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ አስተባባሪ አካላት አደጋው የተከሰተበት ቦታ በመሄድ ተጎጂ ቤተሰቦችን ጎብኝተዋል።
አስተባባሪ አካላት የአደጋው ሰላባ የሆኑ የቤተሰብ አባላትን በጎበኙበት ወቅት በተራራማ አከባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ አባላት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
የአደጋው ሰለባ የሆኑት አርሶአደር ዘይኔ ጁቤር በመኖሪያ ቤቱ እስከ ስድስት የሚሆኑ የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ እንሰሳት የሚኖሩ እንደነበርና በአደጋው ወቅት የቤተሰብ አባላቱ በእንቅልፍ ላይ ሆነው እንደነበር ገልጸው በሰአቱ ባሰሙት የይድረሱልኝ ጥሪ የአከባቢው ማህበረሰብ ተረባርቦ ሰውንና እንሰሳት ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል።
እንደወረዳ አስጊ ናቸው ተብለው የተለዩ አምስት ቀበሌዎች መኖራቸው የተገለጸ ሲሆን የግንዛቤ ማስጨበስና የጥንቃቄ መልዕክት ስራዎች በየጊዜው እየተሰሩና መሆናቸውን በመጥቀስ፦
ከዚህ ጎን ለጎን ችግሩን በዘላቂነት እስኪፈታ ጊዜያዊ የመፍትሄ አማራጮችን በመፈለግ መሆኑንና በተያዘው ዓመትም እስከ አራት የሚሆኑ አባወራዎችን ከስጋት ነፃ የሆኑ ቦታዎች ተለይተው አደጋውን የመቀነስ ስራ መሰራቱን ከወረዳው የአደጋ ስጋትና ቅድመ መከላከል የገኘነው መረጃ ያመልክታል።
መረጃው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ነው!