ሆሳዕና፣ጥቅምት 9/2017 በክልሉ የወባ በሽታን ለመከላከል 1ነጥብ 2 ሚሊየን የአልጋ አጎበር መሰራጨቱም ተመላክቷል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በክልሉ የወባ በሽታ ተጋላጭነትን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ሆሳዕና፣ጥቅምት 9/2017 በክልሉ የወባ በሽታን ለመከላከል 1ነጥብ 2 ሚሊየን የአልጋ አጎበር መሰራጨቱም ተመላክቷል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በክልሉ የወባ በሽታ ተጋላጭነትን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ የወባ በሽታን ለመከላከል 1ነጥብ 2 ሚሊየን የአልጋ አጎበር መሰራጨቱን የተናገሩት አቶ ሳሙኤል ለወባ በሽታ ተጋላጭ በሆኑ በ31 ወረዳዎች ደግሞ 120 ቀበሌዎችን መሸፈን የሚያስችል የጸረ ትንኝ ኬሚካል ርጭት መካሄዱን አብራርተዋል።
ለትንኝ መራቢያነት አመቺ የሆኑ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስ እና የማዳፈን ስራ እየተከናወነ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
የክረምቱን ወራት መውጣት ተከትሎ የወባ ተጋላጭነት እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው ከክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ጀምሮ በየደረጃው ያለው አመራር የችግሩን አሳሳቢነት ለመከላከል ዘርፈ ብዙ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ሀላፊው በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
የወባ በሽታ በምርታማነት ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው ያሉት ኃላፊው ህብረተሰቡ ስለበሽታው ያለውን ግንዛቤ ለማዳበር እየተሰራ ነው ብለዋል።
የወባ በሽታ በህብረተሰቡ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመከላከል የምርመራ እና የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው ያሉት ኃላፊው ችግሩን ለመቅረፍ የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።
የሀይማኖት ተቋማት ከህብረተሰቡ ጋር ባላቸው መስተጋብር ስለ በሽታው አስከፊነት እና በመከላከያ መንገዶች ዙሪያ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ ሚናቸውን እየተወጡ ስለመሆኑም አቶ ሳሙኤል በመግለጫቸው አብራርተዋል።
ህብረተሰቡ ስለበሽታው አስከፊነት መዘናጋት እየታየበት ነው ያሉት አቶ ሳሙኤል ትኩሳት እራስምታት፣ብርድ ብርድ ማለት እና ሌሎች ተዛማጅ የበሽታው ምልክቶች ሲታዩ ፈጥኖ ወደ ጤና ተቋማት መሄድ እንዳለበት ጠቁመዋል።
በክልሉ ያሉ የጤና ተቋማት 24 ሰዓት ዝግጁ ሆነው የህክምና አገልግሎት እየሰጡ ስለመሆኑም አቶ ሳሙኤል በመግለጫቸው አስረድተዋል።
በዘርፉ የሚደረገውን ሁሉን አቀፍ የህክምና አገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ በሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች የድጋፍና ክትትል ቡድን ተቋቁሞ እየተሰራ ስለመሆኑም አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል።
በክልሉ የወባ ስርጭትን ለመከላከል በተሰራባቸው አካባቢዎች የተሻለ ለውጥ እየመጣ ነው ያሉት ኃላፊው ህብረተሰቡ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማዳፈን እና የማፋሰስ ስራ ማጠናከር እንዳለበትም ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።
ለክ/መ/ኮ/ጉ/ቢሮ ዘገባ
የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ