በስልጢ ወረዳ በሁሉም ቀበሌያት የወባ በሽታ ስርጭት የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር ህብረተሰቡን አሳታፊ ባደረገ መልኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል ።
በአገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ቁጥር አንድ የሰው ልጆችን ገዳይ በሽታ እንደሆነ የሚታወቀው የወባ በሽታ በወረርሽኝ መልክ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ለብዙሃን ሞት ምክንያትም ሆኗል፡፡
በሽታው በአገር ኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ኑሮና በፖለቲካው ላይ የሚያስከትለው ቀውስ በቀላሉ የሚገመት አይደለም ስለሆነም በሽታው በአብዛኛው በህፃናት፣ በአረጋዊያንና በነፍሰጡር እናቶች ላይ ይበልጥ መታየቱ በአሳሳቢነቱ ይወሳል፡፡
በጤናው ዘርፍ ትኩረት ከተሰጠባቸው ዋና ዋና የጤና ችግሮች የህብረተሰቡ ጤና ችግር ወደ ማይሆንበት ደረጃ ማድረስ አንዱ ወባን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር ብሎም ወባን ፈጽሞ ማስወገድ የሚል ግብ መሆኑ ይታወቃል ፡፡
የአየር ንብረት ለውጥን ተከትለው የሚከሰቱ የጤና ችግሮች የዝናብ ስርጭትና የአየር ሙቀት ሁኔታ ከመደበኛው በተለየ መልኩ የተዛባ በመሆኑ ለወባ ወረርሽ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
ህብረተሰቡ በሽታንም አስቀድሞ የመከላከል አቅሙን ማሳደግ ይቻል ዘንድ የተጠናከረና ቀጣይነት ያለው በመሆኑ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ያለው የወባ በሽታ ወረርሽኝ በተመለከተ የአጎበር ስርጭት የኬሚካል ርጭት ስራዎችን የወባ በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ስራ ውጤታማ እንዲሆን ህብረተሰቡን የቁጥጥር ስራው ባለቤት በማድረግ አቀናጅቶ በመስራት የወባ በሽታ ጤና ላይ የሚደርሰዉን ተፅዕኖ መቀልበስ የጋራ ጥረትን እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል ።
ለስ/ዞ/ጤ/መም/ዘገባ
የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ