Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

መገናኛ ብዙሀን ለህብረተሰቡ ወቅታዊ መረጃን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ

መገናኛ ብዙሀን ለህብረተሰቡ ወቅታዊ መረጃን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ወቅታዊ የወባ በሽታን አስመልክቶ ከሚዲያ አካላት ጋር በወራቤ ከተማ ውይይት አካሄደ።

የማዕከላዊ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አማካሪ አቶ ሀብቴ ገብረሚካኤል እንደሀገር እና ክልል የተከሰተው የወባ ወረርሽኝ የህብረተሰቡ ጤና ስጋት እንዳይሆን ማህበረሰቡን የማንቃት ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ክልሉን እንደ አዲስ ከማደራጀት ጎን ለጎን በክልሉ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን የመከላከል ስራ ቢሮው በትኩረት መሰራቱን ገልጸዋል።

የማህበረሰቡን ቋንቋ ተጠቆሞ ሚዲያው ወቅታዊና ተዓማኒ መረጃዎች ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡን በማንቃት የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በሀገር አቀፍ ደረጃ ወረርሽኞች መነሻ የሚያደርጉት ማህበረሰቡ ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠቱ ነው ብለዋል።

ወባ በሀገራችን የቆየ በርካታ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ትኩረት መስጠት የሚገባው በሽታ ነው።

በየአካባቢው ለወባ ወረርሽኝ መባባስ የአየር ንብረት ለውጥ ፣ የህብረተሰቡ መዘናጋት እና የአካባቢ ጽዳት ትኩረት ማነስ መሆኑን ተናግረዋል።

ወረርሽኙን ለመከላከል ቢሮው ህብረተሰቡን የማንቃት የአጎበር ስርጭት ፣ የፀረ ወባ ኬሚካል ርጭት እና ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን ስራ በክልሉ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ 1ሺ 692 ጤና ተቋማት መኖራቸውን ያነሱት አቶ ማሙሽ አስካሁን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ አጎበር ስርጭትና በ31 ወረዳዎች የፀረ ወባ ኬሚካል እርጭት መከናወኑን ገልፀዋል።

በዚህም የወባ በሽታ የሚያስከትለውን ህመምና ሞት በክልሉ መቀነስ ተችሏል ብለዋል ።

በነባራዊና አሁናዊ የወባ ሁኔታ እና ወባን መከላከልና መቆጣጠር ረገድ የሚዲያው ሚና በሚል የተዘጋጀ ሰነድ በአቶ ሳሙኤል ሀይሉ እና ወይዘሮ ዝናሽ ደለለኝ አማካይነት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ተቋሙ ለሚዲያ ተቋማት ወጥነት ያለው መረጃ ልውውጥ መስጠት ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚገባው ተናግረዋል።

በኤልያስ ቲርካሶ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *