Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በዋና ዋና እና ቁልፍ የጤና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ እና የማኔጅመንት አካላት የዞን ጤና መምሪያ እና የልዩ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ባለድርሻ አካላት እንዲሁም አጋር ድርጅቶች በተገኙበት በዋና ዋና እና ቂልፍ በሆኑ የጤና ጉዳዮዮች ላይ ምክክር የሚደረግ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገልጿል።

አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ ከቢሮ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ የ3 ዓመታት ዕቅድ ተፈጻሚ መደረጉን በመግለጽ የቀሪ 7 ዓመታት ስትራቴጂክ ዕቅድ በማቀድ ወደ ስራ መገባቱን በማውሳት በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰቱ ወረርሽኞች በማህበሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

የአየር ንብረት ለውጡን እና መጪውን ክረምት ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ጭምር ታሳቢ ያደረገ ለወረርሽኝ የማይበገር እና የማይንገራገጭ የጤና ስርዓትን መገንባት እንደሚገባ የገለጹት አቶ ሽመልስ በእናቶች እና የህጻናት ጤና እንዲሁም ቁልፍ በሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ የሚመክረው የውይይት መድረክ በውይይቱ ወቅት በሚለዩ ጉዳዮች ወቅቱን የጠበቀ ግብረ መልስ በመስጠት ማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የእናቶችና ህጻናት እና የስርዓት ምግብ ከማሻሻል እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት ከማጠናከር አኳያ ተግባራት በተሻለ ደረጃ መከወናቸውን ሀላፊው አክለው ገልጸዋል::

የክልሉ የ11 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት አየቀረበ ሲሆን የውይይት መድረኩ ከሚቀርቡ ሪፖርቶች መነሻ አንኳር በሆኑ ጉዳዮች አጽንኦት ሰጥቶ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *