Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የቤተሰብ እቅድ ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የአመራሩ ሚና ወሳኝ ነው!” በሚል መሪ ቃል በሆሳዕና ከተማ የአድቮኬሲ መድረክ ተካሄደ።

የጤና ሚኒስቴር፣ የክልሉ ጤና ቢሮ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ በጋራ ያዘጋጁት አቶ ግዛቸው ዋሌራን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት የቤተሰብ እቅድ ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የአመራሩ ሚና ወሳኝ ነው !” በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሆሳዕና ከተማ የአድቮኬሲ የውይይት መድረክ መካሄዱም ታውቋል።

በጤና ሚኒስቴር የሚኒስቴር ዴኤታው የጤና አገልግሎት ፕሮግራም ዘርፍ ከፍተኛ አማካሪ ፕሮፌሰር ስለሺ ጋሮማ ኢትዮጵያ በ2030 እውን ለማድረግ የያዘችው ግብ ለማሳካት የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥራት ያለው የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት በክልሉ ተደራሽ እንዲሆን በተለይም በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የኃይማኖት ተቋማት ለተግባሩ ተፈፃሚነት የሚጠበቅባቸውን ትልቅ ሚና ሊወጡ እነደሚገባ ተናግረዋል።

አገራችን አሁን ካለችበት 41 በመቶ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተደራሽነት 54 በመቶ ለማድረስ በቁርጠኝነተ እየተሰራ እንደሆነ የገለጹት ፕሮፌሰር ስለሺ ለዚህም ክልሎች መደበኛ በጀት በመመደብ ተግባራትን የማሳለጥ ስራዎች በመስራት እንደ ሀገር በሚከወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ የእናቶችና የወጣት ሴቶችን ሚና ከፍ ያለ እገዛ እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ም/ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ በቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተግባራትን በአግባቡ መፈጸም ከሚያስገኛቸው ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች ባሻገር የእናቶች እና ህፃናት ሞት በመቀነስ ረገድ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተደራሽነት ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ያመላከቱት አቶ አሸናፊ ለወጣት ሴቶች የስነ-ተዋልዶ አገልግሎቶችን ግንዛቤ በማሳደግ እድሜያቸው ከ15-19 እድሜ ክልል ውስጥ ላሉና ላገቡ ወጣት ሴቶች የብልህ ጅምር /Smart Start / ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ኢትዮጵያ የዛሬ ሰባት ዓመት ለመድረስ የያዘችውን ግብ ስኬታማ ለማድረግ 54 በመቶ ጥራት ያለው የቤተሰብ እቅድ አገለግሎት እውን እንዲሆን በየዓመቱ 1.83 በመቶ መጨመር ተጠባቂ መሆኑን የቀረበው ሰነድ ያስረዳል።

ሁሉም ክልሎች ለቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ስራዎች የበጀት ኮድ ሰጥቶ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው ከዚህ ቀደም ውይይት ተደርጎበት ውሳኔዎች መተላለፋቸውን እና በዚህ የንቅናቄ መድረክ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ም/ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና በየደረጃው ያሉ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ሀላፊነት በመውሰድ ለስራ ተግባራዊነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ተጠይቋል።

የቤተሰብ እቅድ ጥራትን ለማረጋገጥ በክልሎች ውስጥ ያለውን ተደራሽነት ተፈጻሚ ለማድረግ የአድቮኬሲ እና የንቅናቄ ስራዎች በሌሎች ክልሎች ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል።

የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *