የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ወቅታዊ የወባ ሁኔታን እና የሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀት የተመለከተ ግምገማ አካሂዷል።
የዞኑ ጤና መምሪያ በየሳምንቱ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ስርጭት ለመግታት በበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ መስጠት ዳሬክቶሬት የተዘጋጀ ሰነድ በአቶ ዳርኬላ ሲርጀባ ቀርቦ ከሚመላከታቸው የዘርፉ ባለሞያዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው እለት ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱም በባለፉት አራት ሳምንታት የወባ በሽታ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣ መሆኑን በመግለጽ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚያስችሉ የመከላከል ስራዎች የአጎበር አጠቃቀም፣የአቆሩ ውሃዎችን ልየታ እና የማደፈን ስራዎች፣ የጸረ- እጭ ኬሚካል እርጭት፣የበሽታ ቀኝት እና የክትትል ግምገማ ስርአት ላይ በአግባቡ እየተተገበረ እናዳይደለ በመስክ ምልከታ መታየቱን በመግለጽ በቀጣይ የመከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንዲተገበሩ የመምሪያው ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጌታቸው አሳስበዋል፡፡
የመምሪያው ኃለፊ አክለውም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ከዞን እስከ ቀበሌ ያለ አመራር፣የጤና ባለሞያዎች እና የቀበሌ አደረጃጀቶችን (የሴቶች ልማት ህብረት እና የጎጥ በጎ መሪዎችን) በማቀናጀት ከመቼውም ጊዜ በላይ በቅንጀት መስራት እንደሚያስፈልግ የገለጹ ሲሆን የክልሉም ጤና ቢሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደረግ ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የሴቶች ልማት ቡድን እና 1ለ5 አደረጃጀትን በአዲስ መልክ በሴቶች ልማት ህብረት እና የ1ለ10 የማደራጀት ተግባር ያለበትን ደረጃ እና የአተገባበር መመሪያ በዞኑ ሴቶች እና ህጻናት መምሪያ ከፍተኛ ባለሞያ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን ያልተደራጁ አባላትን ሙሉ በሙሉ እንዲደራጁ እና የተደራጀ አባላትን ደግሞ አቀናጅቶ በመጠቀም በጤናው ዘርፍ የተሸለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል ፡፡
በውይይቱም የዞን ጤና መምሪያ ማኔጅመንት አባላት፣የዞን እና የወረዳ ሴቶች እና ህጻናት አመራሮች እና ባለሞያዎች፣የዞን እና የወረዳ ሴቶች ሊግ እና ሴቶች ፌዴሬሽን፣የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ መስጠት አስተባባሪዎች እና የጤና ጣቢያ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ለሀ/ዞ/ጤ/መ/ ዘገባ
የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ