ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ገምግማ ማካሄዱን የማዕከላዊ ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ ገልጿል።
ሳምንታዊ የክንውን ሪፖርት እና የቅኝት ምላሽ አሰጣጥ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል ።
7,065 የወባ በሽታ ኬዝ ሪፖረት መደረጉን እንዲሁም የወባ በሽታ ከባለፈው ሳምንት በ23/% ጭማሪ ማሳየቱን እና በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ አየጨመረ መምጣቱን ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል።
እንደ ክልል በአንድ ወር ውስጥ 22,939 የወባ በሽታ ኬዝ ሪፖርት የደረገ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የምላሽ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አመላካች መሆኑም ተገልጿል።
በምግብ እጥረት የተጎዱህጻናትና እናቶች ልየታ ላይ ጉድለት መኖሩን፣ የቀረበው ሪፖርት የሚያመላክት ሲሆን የምግብ እጥረት፣ የኩፍኝ በሽታ፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፣ የእናቶች እና የህጻናት ጤና፣ የኤች አይቪ ኤድስ ምርመራ አገ/ት የኩፍኝ በሽታ፣ የእከክ በሽታ፣ የቲቢ በሽታ፣ እና ሌሎች በሽታዎች ዝርዝር ሳምንታዊ ሪፖርት ቀርቧል።
የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ የወባ በሽታ ከፍተኛ ጫና ያለባቸው የክልሉ አካባቢዎች ላይ ያሉ ትክክለኛ መረጃዎችን ምልከታ በማድረግ በቅንጅት የመከላከል ተግባራትን በማጠናከር ከአጎበር አጠቃቀም እንዲሁም ከላብራቶሪ ምርመራ ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮች በጥራት ስለመፈጸማቸው ክትትል ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል።
ጥራት ያለው እና ለውሳኔ የሚጠቅም መረጃን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ተግባራት ልዩ ትኩረት እንደሚሹ የጠቆሙት አቶ ሽመልስ የአጣዳፊ ስርዓተ ምግብ ችግር ያለባቸው እናቶች እና ህጻናት ልየታ ስራዎችን በየደረጃው ያሉ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት እና በሀላፊነት ተግባሩን ሊደግፉት እንደሚገባ በመግለጽ ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ የሆኑ ቀበሌያ ወደኋላ እንዳይመለሱ ሁሉም ባለድርሻ አካል አይተኬ ሚናውን እንዲወጣ በመጠየቅ በቀጣይ ሳምንት ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ስራዎች የተግባር ዕቅድ በማውጣት መፈጸም እንደሚገባ ገልጸዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ የውሃ ማከሚያ መድሀኒት ስርጭት ስራዎች በሂደት ላይ መሆኑን ጠቅሰው በጀት ዓመቱ የክልሉን 200 ቀበሌያት ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚሰራው የኤች አይቪ ኤድስ ምርመራ አገ/ት ስራ በተጠናከረ መልኩ በመተግበር የሚጠበቀውን ውጤት የማምጣት ሂደቶችን አጎልብቶ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
እየጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ጫና ከማስቀረት አኳያ የመከላከልና የቁጥጥር ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ እንዲሁም ከምግብ እጥረት ልየታ ጋር ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ እናቶችና ህጻናት ከምግብ እጥረት በሽታ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የጤና ችግር ሰለባ እንዳይሆኑ አየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖራቸውን አቶ አሸናፊ አክለው ገልጸዋል።
የማ/ኢ/ክ/ የህ/ጤ/ኢንስትቱዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ በበኩላቸዉ በክልሉ አንዳንድ አካባቢ እየጨመረ የመጣው የወባ በሽታ ላይ ያሉ መሠረታዊ ችግሮችን በመለየት ከፍተኛ አመራሮች ድጋፍና ክትትል ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቁመው ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ላይም የአካባቢ ቁጥጥር እና የመከላከል ተግባራትን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።
እየጨመረ የመጣው የተወሳሰበ የምግብ እጥረት በሽታ ልየታ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ያመላከቱት አቶ ለገሰ የውሃ ህክምና ስራዎችን በማጠናከር ወጥ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ከሴክተር መ/ቤቶች ጋር ያሉ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ጥራት ያለው የተናበበ እና ታዓማኒነቱ የተረጋገጠ መረጃ ልውውጥ ስርዓቱን ማሳለጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የወባ በሽታ እና የምግብ እጥረት በሽታ መጨመር ጋር ተያይዞ ችግር ፈቺ የሆነ የምላሽ ስራዎችን መፈጸም የወባ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ በጨመረባቸው የክልሉ አካባቢዎች ልዩ ድጋፍ በሚደረግበት ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ የመከረው የውይይት መድረክ የወባ በሽታ መከላከያ መድሀኒት ርጭት በአንዳንድ አካባቢዎች መጀመር የበሽታውን ጫና ከመቀነስ ረገድ ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን አስምሮበታል።
የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ