Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተቋሙን የ10 ወራት አፈፃፀም በዛሬው እለት በወራቤ ዩኒቨርስቲ እየገመገመ ይገኛል ።

ጤና ኢንስቲትዩቱ የ2016 በጀት ዓመት የአስር ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የቢሮው ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወራቤ ዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ዉስጥ እያካሄደ ነው።

ኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ የአፈፃፀም ሪፖርቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በጤናው ዘርፍ የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሻሻል ባለፉት አስር ወራት የተሰሩ ተግባራትንና ጉድለቶች ላይ መምከር እንደሚገባ ገልፀዋል።

የቢሮው የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት በጤናው ዘርፍ በርካታ ተሞክሮ ሊቀመርባቸው የሚገቡ ተግባራት መከናወን የተቻለ መሆኑን ጠቅሰው ድንገተኛ አደጋዎች ላይ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጠንካራ ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በክልሉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች መበራከታቸውን ገልፀው በዋናነትም የኮሌራ፣ የኩፍኝ እና የወባ ወረርሽኞች እንዲሁም የጎርፉ አደጋ መኖሩን ተከትሎ ችግሩን ለመቀነስ እጅግ ጠንካራ ተግባራት መከናወናቸውን እና የላብራቶሪ ተግባራት ተደራሽነቱ ከዚህ የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል ።

የጥናት እና ምርምር ስራዎች በጥሩ መልኩ እየተካሄደ እንደሚገኝ ያወሱት ዳይሬክተሩ የመረጃ ስርዓታችንም ለሌሎች ምርጥ ተሞክሮ እንደሚሆን ለማስቻል በጥራት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

በአጠቃላይ ይህ መድረክ በቀሪ ጊዜያት ዉጤታማ ስራ እንድንሰራ ያግዘናል ብለዋል ዳይሬክተሩ ።

በጤናው ዘርፍ ለማህበረሰቡ ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የዘርፉ ባለሙያዎች የሰሯቸውን ስራዎች የአፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበው ዉይይት እየተደረገባቸው ይገኛል ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *