Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በጄኔቫ ስዊዘርላንድ ሲካሄድ የነበረው 77 ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ በ2005 ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulations 2005 ) ላይ የተደረገዉን ማሻሻያ በማጽደቅ ተጠናቋል።

በጄኔቫ ስውዘርላንድ የአባል አገራትን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ ሲካሄድ የነበረው 77 ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ በ2005 ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulations 2005 ) ላይ የተደረገዉን ማሻሻያ እና ሌሎች የመፍትሄ ሀሳቦችን ( Resolutions) በማጽደቅ ተጠናቋል።

ሃገራችን የአፍሪካ ቡድንን በማስተባበር የጋራ አቋም እንዲያዝና በቀረቡት ማሻሻያዎች ውስጥ ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማሳደግ ለታዳጊ ሃገራት ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ ማሻሻያዎች እንዲጸድቁ ከፍተኛ አስተዋጾዖ ያበረከተች ሲሆን የሃገራትን ሉዓላዊነት የሚጋፉና በተለይም በአፍሪካ ሃገራት ላይ የንግድና ትራንስፓርትና ኢኮኖሚ ረገድ አስገዳጅ ግዴታዎች የሚጥሉ ሃሳቦች እንዳይካተቱ ማድረግ ተችሏል፡፡

ከ300 በላይ ፕሮፓዛል በአባል አገራት ቀርቦ ማሻሻያ ተደርጎ የፀደቀዉ ዓለምአቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulations 2005 ) በዋናነት በህብረተሰብ ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ወቅት የሀገራት ዝግጁነትና ምላሽ አሰጣጥ አቅምን ለማሻሻል እንዲሁም አለም አቀፍ ወረርሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ታሳቢ ያደረገ ነዉ። በዚህ መሰረት ተሻሽሎ የጸደቀው የዓለም አቀፍ የጤና ደንብ ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋና ወረርሽኝ ሲከሰት ፍትኃዊ የሆነ የህክምና ግብዓት ተደራሽነት እንዲኖርና መሰረታዊ የሆኑ የህብረተሰብ ጤና አቅም ለማዳበር የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍ በተለይም ለታዳጊ ሃገራት ለማሰባሰብ እንዲቻል አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ መሆኑም ተገልጿል።

በጉባኤዉ ማጠቃለያ ላይ የአፍሪካ አባል ሀገራትን በመወከል ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ማሻሸያ ተደርጎበት የፀደቀዉ ይህ ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ አገራት ከተባበሩና በጋራ ከሰሩ ለጋራ ዓላማ በጋራ መቆም እንደሚቻል አይነተኛ ማሳያና ምስክርነት መሆኑን በማበከር ደንቡ ለድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ወረርሽኝ ቅኝትና ቁጥጥር ፣ዝግጁነት እንዲሁም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እጅጉን እንደሚያግዝ ገልጸዋል። ይህ እዉን እንዲሆን ላለፉት 2 ዓመታት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል።

በሌላ በኩል አገራት ለህብረተሰብ ድንገተኛ ጤና አደጋዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዲችሉ ፣ እንዲሁም ቀጣይነት ያለዉ ጠንካራ የጤና ስርዓት እንዲኖራቸዉ የሚያግዙ ሌሎች የመፍትሄ ሀሳቦችና ውሳኔዎች (Resolutions) በጉባኤዉ ቀርበዉ ፀድቀዋል።

በስዊዘርላድ ጄኔቫ ሲካሄድ በነበረዉ 77ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ የተሳተፈዉ የኢትዮጵያ ልዑክም ወደ አገር ውስጥ የተመለሰ ሲሆን የ 155ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በክብርት የጤና ሚኒስትሯና የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ተሳትፎ እየተደረገበት ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *