Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ወቅት ነባራዊ ሁኔታዎች እና የተሰጡ ምላሾች ላይ ያተኮረ ውይይት መደረጉ ተገለጸ።

ኳሊቲ ሄልዝ ኬር አክቲቪቲ ፕሮጀክት ከሚደግፋቸው የሀዲያ ዞን 3 ወረዳዎች እንዲሁም ከጉራጌ ዞን 1 ወረዳ ላይ የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የተከናወኑ ተግባራት አንዲሁም የተሰሩ የምላሽ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው እለት በሆሳዕና ከተማ መደረጉን የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ገልጿል።

የክትባት አገ/ት ጥራትና ደህንነትን የማሰ ጠበቅ ፋይዳና አገ/ት አሰጣጥ ላይ ያሉ የአፈጻጸም ጉድለቶችን ለማረም የሚያስችል መግባባት ላይ ለመድረስ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑም ተገልጿል።

የማ/ኢት/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤናና ጤና-ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም ጥራት ያለውና ፍትሀዊ የጤና አገ/ት ተደራሽ ለማድረግ የክትባ ጥራትን ማስጠበቅ ተገቢ ነው ብለዋል።

በጤና ተቋማት የሚሰጡ የክትባት አገልግሎቶች ጥራትና ደህንነታቸው ተጠብቆ ተደራሽ በማድረግ ረገድ የጤና ኤክ/ን ባለሙያዎች የጤና ባለሙያዎች የሚያበረክቱት አሰተዋጽኦ ጉልህ ፋይዳ ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ልዩ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አቶ ወልደሰንበት አክለው ገልጸዋል።

በክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች፣ ሕጻናትና ሥርዓተ-ምግብ አገልግሎቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሌጂሶ የክትባትን ጥራት ለማስጠበቅ በየወቅቱ የተሰጡ ሥልጠናዎች ያመጡት ውጤት ላይ ተገቢው ክትትል ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡

ስለክትባት አገ/ት ለተለያዩ ባለድሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት የማህረሰቡ ንቃተ ጤና ከፍ እያለ መምጣቱን የጠቆሙት አቶ ተስፈዬ መሠረታዊ የሆነ የባህሪ ለውጥ ለማምጣት የተለያዩ አደረጃጀቶችንና ተጽእኖ ፈጣሪ አካላትን እንዲሁም ምቹ አጋጠማቸዎችን በመጠቀም አጠናከሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በ22 ወረዳዎች መከሰቱን ከቀረበው ሰነድ መረዳት የተቻለ ሲሆን ከክልል ጤና ቢሮ እስከታችኛው መዋቅር በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ባደረጉት ርብርብ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያስከትል የነበረውን የጤና ጉዳት እና ሞት መቀነስ መቻሉም ተገልጿል።

የክትባት ጥራት ላይ ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ በክትባት ተደራሽ የሚደረጉ ታላሚዎች ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ ክትባት እንዲያገኙ በማድረግ ፍትሀዊ የሆነ የጤና አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ጠይቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚያመላክተው የፖሊዮ በሽታ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን መነሻ በማድረግ የክትባት አሰጣጥ ሥርዓቱን ማጠናከር ይገባልም ተብሏል፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያም በጋምቤላ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች አዲስ በፖሊዮ በሽታ ወረርሽኝ የተያዙ ሰባት ሰዎች መገኘታቸውን መረጃዎች የሚያመላክቱ ሲሆን ሥርጭቱን ለመግታትና ለመቆጣጠር መረባረብ እንደሚገባ የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት መልዕክት የሚጠቁም በመሆኑ የቅድመ መከላከል ስራዎችን ማጠናከር አንደሚገባ ተገልጿል ፡፡

ባለፉት ጊዜያት በተለያዩ የክልላችን አካባቢዎች የተከሰቱ ወረርሽኞች ካስከፈሉት ዋጋ ትምህርት በመውሰድ የቅድመ መከላከል ስራዎችን አጠናክሮ ለወረርሽኝ የማይበገር የጤና ስርዓት መገንባት ይገባልም ተብሏል።

የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *