በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጤና ዘርፍ የተከናወኑ ያሉ ስራዎች በተመለከተ የክልል ምክር ቤት ከማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመቀናጀት በሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ ህዝባዊ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በውይይት መድረኩም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ የምክር ቤቱ ምክትል አፈጉባኤ ወ/ሮ መነቴ ሙንዲኖ የምክር ቤቱ ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ የሾኔ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና ከባዳዎቾ ወረዳ የመጡ ባለድርሻ አካላት ታድመውበታል።
በክልሉ ጤና ቢሮ የተዘጋጀው የመወያያ ጽሁፍ ቀርቧል።
የእናቶች ጤና አገልግሎት ስራዎች፣ የጤና ኤክስቴንሽን መቀዛቀዝና ስርዓተ ምግብ እና የተለያዩ ተላላፊ በሽታ ችግሮች በአግባቡ ከመምራት አኳያ ችግሮች እንዳሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ የውይይት መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት ተናግረዋል።
በጤና ስርዓቱ ያሉ ችግሮች በአፋጣኝ መፍታት እንደሚገባ ተገልጿል።
ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ተወካዮች በክልሉ የሚገኘው የጤና ስርዓት መስተካከል የሚገባቸውን ጉዳዮች በመነሳት ላይ ይገኛል።ምንጭ ደሬቴድ