Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በበየሳምንቱ ለሚሰበሰቡ መረጃዎች ትረጉም እየተሰጠ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ተገለፀ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን ጤና መምርያ 45ኛ ሳምንት የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል(EOC) ዉይይት የመምርያው ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በተገኙበት በቀን 05/09/2016 ዓ.ም ያካሄደ ሲሆን፡-

በሳምንቱ በቅኝት ስር ሪፖርት ከሚደረጉ በሽታዎች እንደ ወባ እና የምግብ እጥረት፤ ከመረጃ ጥራት ጋር ተያይዞ እንደ ሪፖርት ምሉዕነት እና ወቅታዊነት እንዲሁም ደግሞ በመረጃ ቅብብሎሽ ዙሪያ በስፋት ሪፖርት በመምርያው የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደ/ቅ/ም /ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ በሆኑት አቶ ሳህለ ክብሩ ቀርቦ ሃሳብ አስተያይት ተሰጥቶባቸዋል።

የመረጃ ጥራትን በተመለከተ የሪፖርት ምሉዕነት እንደ ዞን በሳመንቱ 96% እንዲሁም ደግሞ የሪፖርት ወቅታዊት 75% ሲሆን በሳምንቱ ከሪፖርት ወቅታዊነት ጋር ተታይዞ ከሚጠበቀው ቀን ሪፖርት አዘግይተው የላኩ እንደጋኝ፣ እዣ፣ ጌታ፣ ወልቂጤ ከተማ መዋቅሮች መሆኑን ተገምግሟል፡፡

የወባ በሽታ ስርጭት መከላከልና መቆጣጠር ተግባርን በተመለከተ ካለፈው ሳምንት አንፃር ጭማሬ ማሳየቱን ያመላከተው መረጃው በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 537 ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ይህም ከባለፈው ሳምንት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከነበረበት በ 150 ወይም ደግሞ 39 % (በመቶ) ጭማሪ ያሳየ መሆኑን እና ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር በ178 % ጭማሪ ማሳየቱ ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

ለዚህም ከፍተኛ አስታዋፅኦ ያደረጉ ወረዳዎች ወልቂጤ ከተማ (173)፣ አበሽጌ (148)፣ ቸሀ(70)፣ እኖር(65) እና እኖር ኤነር መገር (33) ወረዳ ናቸው፡፡ ሌላው ከ5 ዓመት በታች የስነ ምግብ እጥረት ችግር (የምግብ እጥረት በሽታ) 13 ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ይህም ከባለፈው ሳምንት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከነበረበት በ 13 ወይም ደግሞ 50 በመቶ ቅናሽ ያሳየ መሆኑን እና የዚህ ችግር የህጻናት ልየታ አነስተኛ መሆን ነው፡፡

በሳምንቱ ሌሎች ሪፖርት የተደረጉ ኬዞችና ሞቶች በኬሚካል መመረዝ 05 ሰዎች፣ አዲስ የስኳር በሽታ 7 ሰዎች፣ አዲስ የደም ግፊት በሽታ 29፣ አንድ የማጅራት ገትር በሽታ፣ ደም የቀላቀለ ተቅማጥ 38፣ የእከክ በሽታ 22፣ በሳምንቱ አንዲት እናት እና 04 ጨቅላ ህፃናት ሞት የተመዘገበ መሆኑን ተገምግሟል፡፡

የመምርያው የሚመለከታቸው ስራ ሂደተቶች እና አባለት ጨምሮ ያሳተፈው ውይይቱ የወባ በሽታ የሚጨምርበት ወቅት በመሆኑ በጥብቅ ዲሲፒሊን የሚመለከታቸው ስራ ክፍሎች ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው ፣ የተጀመረው የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ኦዲት ቶሎ እንዲጠናቀቅ፣ ከሌሎች ሴክተር መስርያ ቤቶችና ባለድርሻ አካላት ተቀራርቦ መስራት እንዳለብን አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን በቀጣይም በወረርሽኝ መልክ ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የተለዩት ጎርፍ (Flood)፣ የመሬት መንሸራተት (Land slide)፣ ኮሌራ (Cholara)፣ ወባ (Malaria) የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ተገቢዉን ምላሽ መስጠትና የበሽታ ቅኝቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በመጨረሻም የመምርያው ሀላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በሳምንቱ ሊከናወኑ በሚገባቸው ዝርዝር ተግባራት ለሚመለከታቸው ስራ ክፍሎች ሃላፊነት እና አቅጣጫ ሰጥተው የዕለቱ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC) ዉይይት ተጠናቋል።

ለጉራጌ ዞን ጤና መምርያ ዘገባ

የማ/ኢት/ክ/መ/ ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *