የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የኤች አይቪ ኤድስ በሽታ ቅኝትና ምላሽ ፕሮግራም የ2016 ዓ.ም የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው።
የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የኤች አይቪ ኤድስ በሽታ ቅኝትና ምላሽ ፕሮግራም የ2016 ዓ.ም የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ የክልሉ ጤና ቢሮ ማናጅመንት አካላትና ባለሙያዎች የዞንና የልዩ ወረዳ የዘርፈ ብዙ ኤች አይቪ ኤድስ የመከላከልና የመቆጣጠር አስተባባሪዎች እንዲሁም የዞንና የልዩ ወረዳ የፌም አስተባባሪዎች በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገልጿል።
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገስ ጴጥሮስ ባስተላለፉት መልዕክት የኤች አይቪ/ኤድስ በሽታ ቅኝት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 1,854 ሰዎች አዲስ በኤች አይቪ/ኤድስና በሽታ መያዛቸውን በመጠቆም ወቅታዊ ቅኝት በማድረግ እና ምላሽ በመስጠት የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶች መኖራቸውን አመላክተዋል።
እንደ ሀገር በ2030 አዲስ በኤች አይቪ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ዜሮ ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ሁሉም ባለድሻ አካላት ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የመረጃ አያያዝ እና ልውውጥ እንዲሁም አደረጃጀት ላይ ያሉ ጉድለቶችን ማረም እንደሚገባ ተናግረዋል።
ወቅታዊ ቅኝቶችን መስራት አዳዲስ በኤች አይቪ የሚያዙ ሰዎችን በወቅቱ በማግኘት በሽታው ወደ ሌሎች ሰዎች ከመተላለፉ በፊት ለመቆጣጠር ከማስቻሉ ባሻገር በበሽታው የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ሳይደርስባቸው ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ የህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አቶ ለገሰ አክለው ገልጸዋል።
የተመረጡ ዞኖችና የልዩ ወረዳ እንዲሁም የክልሉ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ