Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የድንገተኛ ጤና አደጋዎች አሰሳና ቅኝት ተግባራት በማጠናከር የድንገተኛ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር እንደሚቻል ተገለጸ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት መሠረታዊ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል(Basic Public Health Emergency Management) የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በወራቤ ዩኒቨርሲቲ CPD ማዕከል መሠጠት ተጀምሯል፡፡

በክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የድንገተኛ ጤና አደጋዎች መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም የስልጠናውን መጀመር አስመልክቶ እንደገለጹት አብዛኛዎቹ ድንገተኛ ጤና አደጋዎች በወረርሽኝ መልክ ስጋት ሊሆኑ ከሚችሉት ጉዳዮች ዋነኛው የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ችግር በሚታይባቸው አካባቢዎች የሚያይል በመሆኑ ማሕበረሰቡን ከከፋ አካል ጉዳት እና ሞት ለመከላከል በየደረጃው የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ተግባራት መጠናከር እንደሚገባቸው ጠቅሰው በዋናነት በማሕበረሰብ, በጤና ኬላዎች እና በጤና ጣቢያዎች እንዲሁም በሆስፒታሎች ጠንካራ የሆነ የበሽታዎች አሰሳና ቅኝት ስርዓት በመዘርጋት የፈጣን ምላሽ ሰጪ ኮሚቴው የተሰበሰቡ መረጃዎችን በመተንተን እና ትክክለኛ መረጃ ለማሕበረሰቡ በማሰራጨት ለውሳኔ መጠቀም እንደሚገባው ገልጸው ለበሽታዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በሁለት ዙር የሚሰጠው ስልጠና በመሠረታዊ የሕብረተሰብ ድንገተኛ ጤና አደጋዎች አሰሳና ቅኝት, በወረርሽኝ ዝግጁነትና ምላሽ , የአደጋ ጊዜ ማገገምን እና ሌሎችንም ርዕሰ ጉዳዮች ያካተተ ሲሆን በክልሉ የሚገኙ የሁሉም ልዩ ወረዳዎች, ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የዞን የጤና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ስራ ክፍል አስተባባሪዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

ዘገባው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *