Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC) የ15ኛው ሳምንት (Epi-week 15/2024) ሪፖርት ግምገማ አካሄደ::

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC) የ15ኛው ሳምንት (Epi-week 15/2024) ሳምታዊ የቅኝት ሪፖርት የገመገመ ሲሆን በበይነ መረብ በቀረበው ሪፖርት የዞንና የልዩ ወረዳዎች ተሳታፊዎች አስተያየት የሰጡ ሲሆን የታዩ ጠንካራና መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች ለይቶ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ደይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም ክልላችን በዚህ ወቅት የወባ፤ የኩፍኝ፤ የኮሌራና የከፍተኛ አጣዳፊ የምግብ እጥረት ወረርሽኞችን በማስተናገድ እንደሚገኝ ገልጸው ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር ከክልል ጀምሮ ርብርብ በማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወነ እንደሆነ ገልጸው በተለይም መጠኑ እየቀነሰም ቢሆን ሙሉ መቆጣጠር ያልቻልነው የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ የተከሰተባቸው ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች መደበኛ ክትባት በማጠናከር፤ ጥራቱን የጠበቀ ክትባት በመስጠት፤ክትባት ያቋረጡትን ለይቶ በማስቀጠል እንዲሁም የተደራሽነት ችግር ያለባቸው አካባቢዎች በመለየት ወረርሽኙን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ቁልፍ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበው ከተከሰቱ ወረርሽኞች ጎን ለጎን የቲቢ እና የኤች አይቪ በሽታዎች በመከላከልና በመቆጣጠር ሂደት ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው በተጨማሪም ከፍተኛ አጣዳፊ የምግብ እጥረት ሕክምናና እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት፤ ነፍሰ ጡርና አጥቢ እናቶች ልየታ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በመግለጽ ከክልል ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ መዋቅሮች ጥራት ያለው መረጃዎችን በወቅቱ በመገምገም የድንገተኛ ጤና አደጋዎች መከላል እና መቆጣጠር እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ዘገባው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ነው፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *