መድረኩ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አቶ ሰለሞን ጉግሳ የጤናው ስርዓት ከሚፈትኑት ዋነኞቹ ጉዳዮች በድንገተኛ ወረሽኝ የሚከሰቱ ችግሮች በመሆኑ በተገቢው የመከላከልና መቆጣጠር ተግባር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
ሃገራችን በተለያዩ ጊዜያት የኮቪድ፤ የኮሌራና ሚዚልና በሌሎች በድንገተኛ ወረሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ ተፈትናለች ያሉት መምሪያ ኃላፊ መሰል ክስተቶች ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጠንካራ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።
በመድረኩ በዘርፉ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች መለየትና መፍታት በሚቻልባቸው መንገዶች በተገቢው የሚመክር መሆኑን አመላክተዋል።
በመድረኩ የዞን የማኔጅመንት አባላት፤ ከወረዳ፤ ከጤና ጣቢያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተወከሉ ተሳታፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።