Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ያሉ የጤና ተቋማት የላቀ የላብራቶር አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ዘመኑን የሚመጥኑ የላብራቶር ምርመራ መሳሪያዎች የማሟላት ተግባር በቀጣይነት እንደሚከናወን የክልሉ ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለፀ።

lab technician operating laboratory devices

የክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ በጤና ተቋማት እየተሰጠ ያለውን የላብራቶር አገልግሎት የላቀ ለማድረግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ህብረተሰቡ ደረጃቸወን በጠበቁ የምርመራ መሳሪያዎች አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች አጋር አካላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ድጋፎችን የማሳለጥ ስራ እየከወነ ሲሆን በዚህም በክልሉ ያለውን የሳንባ ነቀርሳን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል እና የምርመራ አቅምን የበለጠ ሊያሳድጉ የሚችሉ የጂን ኤክስፔርት ማሽኖችን በክልሉ ባሉ የጤና ተቋማት የመትከል እና ስራ የማስጀመር ተግባር ከፌደራል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ባለሞያዎች ጋር በመተባበር እየከወነ መሆኑን ገልፆአል። አገልግሎቱ የሳንባ በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን ከመለየት አልፎ ለበሸታው ህክምና ከሚሰጡ መድኃቶች ውስጥ ፊቱን መድሃኒቶችን ለይቶ የሚያሳይ ከመሆኑም በለይ የሳንባ ነቀርሳ ምርመራ ዘዴ በማሳደግ የበሸታውን ስርጭት ለመግታት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተነስቷዋል።

ምንጭ – የክልሉ ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *