በመቀሌ ከተማ ሲካሄድ የነበረዉ የጤናው ዘርፍ ቅንጅታዊ የጋራ መድረክ ተጠናቋል
___________
የጤናው ዘርፍ የወረዳ ፕላን ያለበት ደረጃ፣ የDHIS 2፣ የዲጅታል ጤና እና Master facility regesartion (MFR ) አተገባበር፣ የተሰብሣቢ በጀት ማስተላለፍ አፈጻጸም፣ የኦዲት ግኝት ሪፖርት፣ የቻናል 2 የፋይናንስ አስተዳደር መመሪያ፣ በማቺንግ ፈንድ የተቀጠሩ ሀኪሞች ፕሮጀክት አፈጻጸም እና የስፔሻሊቲ ትምህርት የሚከታተሉ ሀኪሞች አፈጻጸም እንዲሁም ከተጠሪ ተቋማት የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ ህብረተሠብ ጤና ኢንስቲትዩት በወረርሽኝ ላይ የተጠኑ ጥናቶች ግኝት፣ እንዲሁም የህብረተሠብ የጤና አደጋና ምላሽ አሰጣጥ አሁናዊ ሁኔታ በሚሉ ርእሠ ጉዳዮች ላይ የቀረቡ ገለጻዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎ ከተገመገመ በኃላ በከፍተኛ አመራሩ ቀጣይ አቅጣጫ ተሰቷል።
ዶክተር መቅደስ በውይይት ወቅት እንደተናገሩት የቀረቡ አስተያየቶች በግብረመልስነት ተወሰደው የእቅድ አካል ተደረገው የሚተገበሩ ይሆናል ያሉ ሲሆን ስራዎቹ ከሚኒስትር መ/ቤቱ ቡድን ተደራጅቶ ወደ ክልል በመላክ በጋራ የሚከናወኑ መሆኑን፣ ክልሎችና ተጠሪ ተቋማት በባለቤትነት ወስደው ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ዶክተር መቅደስ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር፣ የአደጋ መከላከል ዝግጁነት ስራው ትልቅ ትኩረት ተሠጥቷቸው የሚሰሩ ስራዎች መሆናቸውን ያነሱ ሲሆን የአቅም ግንባታ ስራ ማጠናከር የግል የጤና ተቋማትን በማሳተፍ አብሮ መስራት እንዲሁም በሴክተሩ በአዲስ መልክ የተያዙ ትልልቅ ኢኒሼትፎች እንደ የጤናዉ ዘርፍ የአገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ፣ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በመጨመር ጽዱ የጤና ተቋማት መፍጠር፣ የሜዲካል ቱሪዝም ማሳደግ እና የሲቭል ሰርቭስ ሪፎርምን ሀላፊነት በተሞላ መንፈስ መምራት ላይ በትኩረት እንዲሠራ አቅጣጫም ሠጥተዋል።
በስብሰባዉ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ማህበራዊ አገልግሎቶች ሽግግር ሰክሬታሪያት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ክልሉ የጤና አገልግሎት አፋጣኝ ድጋፍ ከጤና ሚኒስቴር ማግኘቱን የተናገሩ ሲሆኑ ለዚህም ክልሉን በመወከል ለጤና ሚኒስቴር ምስጋና አቅርበዋል።
የትግራይ ክልል ጤና ሲጠበቅ የሌሎች ክልሎችም ጤና ሊጠበቅ እንደሚችል የተናገሩት ፕሮፌሠር ክንደያ ሁሉም ክልሎችና የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።