Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚተገበሩት ማህበረሰብ አቀፍ ተግባራት ከጤና ልማት አጋሮች በሚያስፈልጉ ድጋፎች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚተገበሩት ማህበረሰብ አቀፍ ተግባራት ከጤና ልማት አጋሮች በሚያስፈልጉ ድጋፎች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚተገበሩት ማህበረሰብ አቀፍ ተግባራት ከጤና ልማት አጋሮች በሚያስፈልጉ ድጋፎች ዙሪያ ከጤና፣ከትምህርት፣ከሴቶችና ህፃናት እንዲሁም ከአለም ጤና ድርጅት እና ከአለም አቀፍ ምግብ ፕሮግራም የስራ ሀላፊዎችና ተወካዮች በተገኙበት ነው ውይይቱ የተካሄደው፡፡

ውይይቱን የመሩት በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በመግቢያ ንግግራቸው የክልሉ መንግስት በሚያከናዉናቸዉ የጤና ልማት ስራዎች እና የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ተግባራት ላይ የተሳተፉ የጤና ልማት አጋሮች ለተገኘዉ ስኬት የጎላ ድርሻ እንዳላቸዉ ተናግረው ክልሉ በአዲስ መልክ የተዋቀረ ክልል እንደመሆኑ እና በተለያዩ አካባቢዎች በወረርሽ መልክ የሚነሱ በሽታዎች እንደመኖራቸው ከአጋር አካላት ጋር በቅርበት በመደጋገፍ መስራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ሁሉም የማህበራዊ ዘርፍ ተግባራት ትኩረትን እንደሚሹ በተገለፀበት በዚህ ውይይት በክልሉ ድጋፍ ሰጪ አካላትን በተገቢው ከመጠቀም አንጻር ያለዉን ክፍተት በመቅረፍ በክልሉ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተመላክተዋል፡፡

United Nations office for the coordination of Humanitarian Affairs(OCHA) ካንትሪ ዳይሬክተር ሚስስ ጃይኔን ጨምሮ ሌሎች ተወካዮችና የሀዋሳ ቅርንጫፍ ሃለፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ የጤና ልማት አጋሮችን ባማከለ መልኩ የተገኙት እንግዶች በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎችን በመጎብኘት ትርጉም ያለው ድጋፍ ሊያደርጉ በሚችሉበት አግባብ በቀጣይም በጋራ በመምከር ከድጋፍ አንፃር የተስተዋሉ ጉድለቶችን መቅረፍ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

ከነገ ጀምሮ የተለያዩ በወረርሽኝ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመጎብኘትም የድርጊት መርሀ ግብር በማውጣት የዛሬ የውይይት መድረክ ተጠናቋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *