Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የድንገተኛ ጤና አደጋዎች የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ግብረ-መልስ ግምገማ ተደረገ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የድንገተኛ ጤና አደጋዎች የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ግብረ-መልስ ግምገማ ተደረገ።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ደይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንዲሁም የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች በተገኙበት በወራቤ ከተማ አፈጻጸሙ ተገምግሟል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ደይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ድጋፋዊ ክትትል ድንገተኛ አደጋዎች ከተከሰቱ በኋላ የምላሽ ተግባራት ከማከናወን ይልቅ ቀድሞ መዋቅሮችን በማጠናከር የጤና አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት እንደነዚህ አይነት የድጋፋዊ ክትትል ተግባራት በማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማጠናከር ወረርሽኞችን መቀነስ እንደሚያስፈልግ ገልጸው በየመዋቅሮቹ የታዩ ጠንካራና መሻሻል የሚገባቸዉ ተግባራት ላይ መግባባት ላይ ሊደረስባቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል::

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ በድፋዊ ክትትሉ ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች የተገኙት ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማስፋት ለህዝብ ተጠቃሚነት እንዲዉሉ ያሳሰቡ ሲሆን ከዞን ጀምሮ እስከ ጤና ተቋማት ድረስ የወረርሽኝ ቅድመ ዝግጅት እና ምላሽ ተግባራት ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በድጋፋዊ ክትትሉ ወቅት የታዩ የክህሎት,የእውቀት, የመረጃ አያያዝ እና ሌሎችም ክፍተቶች ለመቅረፍ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸው የገለጹት አቶ ሽመልስ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ የክልሉ ጤና ቢሮ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል ።

በውይይት መድረኩ መዋቅሮችን በመጠናከር ድንገተኛ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት የቅድመ ዝግጅትና መከላከል ስራዎች በማጠናከር ወቅታዊ ድጋፍና ክትትል በማድረግ እና ግብረ-መልስ የመስጠት አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ከድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ አንጻር ትኩረት የሚሹ አካባቢዎችን የመለየት እና ድጋፍ የማድረግ ተግባራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *