Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

ሁለት ራስ ቅል ያለው ልጅ ተወለደ::

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ራስ ቅል ያለው ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

በሆስፒታሉ የህጻናት ህክምና ክፍል ሃላፊ ዶክተር ባሳዝን ጣሰው እንደገለጹት፤ በሆስፒታሉ አንዲት እናት ሁለት ራስ ቅል ያለውን ህጻን ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ገደማ ተገላግላለች።

የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ወላዷ ከአንገቱ በታች በኩል የተያያዘ ሁለት ራስ ያለው ሆኖ የተወለደው ሕፃን ስድስተኛ ልጇ መሆኑን ነው የገለጹት።

እናትም እንዲህ ዓይነት ክስተት መኖሩን ሳታውቅ ቆይታ ለህክምና ከመጣች በኋላ ያወቀች ሲሆን፤ በሆስፒታሉ ሃኪሞች እርዳታ በመለስተኛ ቀዶ ሕክምና መገላገሏን ተናግረዋል።

በትክክለኛ የእርግዝና ወራት ቆይታ የተወለደው ባለ ሁለት ራስ ሕጻን አራት ነጥብ ሁለት ኪሎ ግራም እንደሚመዝንም ገልጸዋል።

የተወለደው ህጻን አሁን ላይ ጤንነት ችግር ባይኖረውም ወደፊት አፈጣጠሩ እክል ሊፈጥርበት እንደሚችል አመላካች ነገሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ነገር ግን ተጨማሪ ምርመራዎች በማስፈለጋቸው የሐኪሞች ቡድን ምርመራና ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ክስተቱ በሆስፒታሉ ታሪክ የመጀመሪያ መሆኑን ጠቅሰው፤ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሚወለዱ ከአንድ መቶ ሺህ ህፃናት መካከል አንድ መሰል ክስተት ሊገጥም ይችላል ብለዋል።

በቀጣይ ሕጻኑ በሚደረግለት ሕክምና ሊለያይ ይችላሉ ይሆን? በሚል ቀረበላቸው ጥያቄ ሁለቱ ራስ አብዛኛውን የሰውነት ክፍል የተጋራ በመሆኑ ሕክምናውን አስቸጋሪ ያደርገዋል ሲሉም ዶክተር ባሳዝን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *