Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አንዳንድ አከባቢዎች የተከሰተው የኩፍኝ ወረርሽኝና ሌሎች የማህበረሰብ ጤና ስጋቶች እንዳይስፋፉ የተጠናከረ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች እየተሰራባቸው መሆኑ ተገልጿል፤

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አንዳንድ አከባቢዎች የተከሰተው የኩፍኝ ወረርሽኝና ሌሎች የማህበረሰብ ጤና ስጋቶች እንዳይስፋፉ የተጠናከረ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች እየተሰራባቸው መሆኑ ተገልጿል፤

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት የ6 ወራት አፈጻጸም ግምገማ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ባደረገዉ የምክክር መድረክ አፅንዖት ሰጥቶ ከመከረባቸው ጉዳዮች መካከል በአንዳንድ አከባቢዎች የተከሰተውን የኩፍኝ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ የተጠናከረ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች እየተሰራባቸው እንደሆነ፡ የኮሌራ ወረርሽኝን ለመቆጠር የተደረገዉ ርብርብና የተጠናከረ የድንገተኛ አደጋዎች አሰሳና ቅኝት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተጠቁሟል።

በምክክር መድረኩ ላይ የክልሉ ጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ተግባራት፣የላቦራቶሪ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እና የጥናትና ምርምር ስራዎች በቢሮዉ ዳይሬክተሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ቀርበዉ ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በክልሉ ባለፉት ጊዜያት ጥራት ያለው የላቦራቶሪ መረጃን ለውሳኔ በመጠቀም ረገድ የተከናወኑ ተግባራት እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ተፅዕኖ ከመቆጣጠር አኳያ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።

የማእከላዊ ኢ/ያ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ
ማሙሽ ሁሴን እና ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ለገሰ ጴጥሮስ የምክክር መድረኩን ዉይይት በጋራ ባወያዩበት ወቅት ባነሱት ሀሳብ በ2016 ዓ.ም በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የወረርሽኝ አደጋዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመተንበይ የዝግጁነትና ምላሽ ዕቅዶችን በማዘጋጀት ወደ ተግባር መገባቱ የወባ፣ የኮሌራ፣ የኩፍኝ በሽታ፣ ያልተመጣጠነ የምግብ እጥረት በማህበረሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት ሳያስከትሉ ለመቆጣጠር ጥረቶች መደረጋቸዉን በመልካም ጎን ቢታዩም
ባለፉት 6 ወራት ወርሽኞችን በስታንዳርድ መሰረት ፈጥኖ ያለመለየትና ፈጣን ምላሽ ያለመስጠት፣ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ያለማጠናከር፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ትኩረት ማነስ፣የሰው ሀይል አለመሟላት እንዲሁም የበጀት እጥረት ችግሮች ማጋጠሙን በመግለጽ ታዓማኒና ጥራት ያለው የላቦራቶሪ ውጤት ያለማግኘት፣ የላብራቶሪ ግብዓት አስተዳደር ላይ ጉድለት መኖር፣ የናሙና ቅብብሎሽ ክትትል ችግር፣ የላብራቶሪ አገ/ት ዘርፍን በአግባቡ ያለመደገፍ፣ ለላብራቶሪ ዘርፍ በቂ በጀት ያለመመደብ ችግሮች ማጋጠማቸውንም አክለው ገልጸዋል።

በወባ፣ በቲቢ፣ እና በኤች አይቪ/ኤድስ ላቦራቶሪ የውጫዊ ጥራት ቁጥጥር አገ/ት በሁሉም የጤና ተቋማት እንዲተገበር በማድረግ በድንገት ለሚከሰቱ ወረርሽኞች የመቆጣጠሪያ ዘዴዎችን በማሳለጥ የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓቱን በአግባቡ በማጠናከር ጥራቱ እና ታዓማኒነቱ የተረጋገጠ የላቦራቶሪ መረጃን በወቅቱ ሪፖርት በማድረግ ህረተሰቡን የጤናው ባለቤት ማድረግ ይገባል ተብሏል።

በክልሉ የሚከሰቱ ድንገተኛ የጤና አደጋዎች በእናቶች እና ህጻናት እንዲሁም በህብረተሰቡ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን የጤና ቀውስ ለመከላከል በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እገዛ ማድረግ እንዲያስችላቸዉ ከቢሮዉ ጋር ተቀናጅተዉ የጥናትና የምርምር ስራዎችን መሰረት ያደረጉ ስራዎች ለመስራት እንዲቻል የመግባቢያ ሰነድ ላይ ተፈራርመዋል፡፡

        የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ

2 Responses

  1. Asrat Kolcha(MpH in Field epidemiology) says:

    Very impressing. Keep it up

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *