Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Month: March 2026

CERPHI

በአፍሪካ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎትን በዲጂታል ለማዘመን የሚያስችል አህጉር አቀፍ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

የጤና ስርዓትን ለማዘመን እና ጥራት ያለው አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሣሪያ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በፕሮግራሙ መክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል። ይህንን አህጉራዊ ራዕይ ከግብ ለማድረስ፣ የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (Africa CDC) ከቴክኒክ ቡድኖች እና አጋር አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጀው “የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ዲጂታላይዜሽን ማዕቀፍ (PHC Digitalization Framework)” ረቂቅ ሰነድ…
Read more

የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ መደበኛ EOC ግምገማ አካሄደ ፡፡

የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጤናና ጤና ነክ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ዳይሬክቶሬት ሳምንታዊ የቅኝት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል ፡፡ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን እንደተናገሩት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚፈጠረዉን የወባ በሽታ ለመግታት ጫናዉ የሚስተዋልባቸውን አካባቢዎችን በመለየት መከላከልን መሠረት ያደረገ የክትትል እና የቁጥጥር ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። ለህብረተሰቡ የወባ…
Read more

ጤና ሚኒስቴር ትብብርን ለማጠናከር እና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የጤና ጉዳዮች እና የጤና ዘርፍ ልማት እና የኢንቨስትመንት ዕቅድ (HSDIP II) ግቦችን ለማሳወቅ ከልማት አጋሮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተድርገዋል።

ሃገራዊ የጤና ዘርፍ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለአጋሮች የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ ወቅታዊ አለም አቀፍ ክስተቶችን ተከትሎ ሊያጋጥሙ የሚችሉ መስተጓጎሎችን ለመቋቋም የሚያስችሉ የመፍትሄ ሀሳቦችን ጨምሮ ትኩረት ሊያገኙ የሚገቡ የጤና ጉዳዮችን አስረድተዋል። ሚኒስትሯ በሚቀጥሉት ዓመታት የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ለመምራት የተነደፈውን የHSDIP II አላማዎችን እና ስትራቴጂካዊ ግቦችን ዘርዝረዋል። ዕቅዱ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማስፋፋት፣ የጤና…
Read more

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወረርሽኝ ቁጥጥር ስራ ውጤት እያመጣ መሆኑ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳወቀ ።

በክልሉ ለሚገኙ ጤና ጣቢያ የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ባለሙያዎች መሰረታዊ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ስልጠና በወራቤ መስጠት ተጀመረ ፡፡ ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በክልሉ የወረርሽኝ ቁጥጥር ስራዎች ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ በጤና ተቋም ያሉ የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ባለሙያ የወረርሽኝ ቁጥጥር ስራን በጤና ተቋም…
Read more

በክልሉ በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎትን 89 % በማድረስ የእናቶችና ህፃናትን ሞት መቀነስ ተችሏል:- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

ቢሮው በጤናውን ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል። የቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንዳሉት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ የማህበረሰቡን ተሳትፎ ማጠናከር ወሳኝ በመሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። በክልሉ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለጤና ተቋማት ግብዓት የሟሟላት ስራ መሠራቱንና ከመንግስት ድጋፍ በተጨማሪ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የግንባታና ግብዓት የሟሟላት ስራ በየአካባቢው እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የመድሀኒት…
Read more

Wellcome Trust’s Delegates Visit EPHI

The Ethiopian Public Health Institute (EPHI) hosted a delegation from the Wellcome Trust, with participation from Resolve to Save Lives, to review Ethiopia’s progress in implementing the 7-1-7 Framework and strengthening national public health systems. During the visit, EPHI’s leadership shared the Institute’s key contributions in laboratory science, research, innovation, and Public Health Emergency Management,…
Read more

የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ( EHAQ) የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሆስፒታሎች ተሸለመ

በሽልማት መርሃግብሩ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ መድረኩ እውቅና የምንሰጥበት እና አዲስ አቅጣጫ የምናስቀምጥበት መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት አዲስ የተገኙ ፈጠራዎች ወደተግባር የሚመጡበት መድረክ መሆኑንም አስረድተዋል። ባለፉት አመታት በሆስፒታል ሪፎርም የተመዘገቡ ውጤቶችን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀምጠዋል። ጥራት መዳረሻ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው እና እየተሻሻለ የሚሄድ መሆኑን ያስረዱት የጤና ሚኒስትር…
Read more

ለኢትዮጵያ የድንገተኛ ህክምና ቡድን (EMT) የአመራር ክህሎት ስልጠና ተሰጠ::

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) ከUK-MED ጋር በመተባበር ከፌዴራል፣ ከክልሎች እና ከመከላከያ ለተውጣጡ 25 የድንገተኛ ህክምና ቡድን አስተባባሪዎች የሰጠው የአመራር ክህሎት ስልጠና ተጠናቋል። ይህ ስልጠና በድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ወቅት የሚሰጠውን የህክምና ምላሽ በብቃት ለመምራት እና የማስተባበር አቅምን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ከUK-MED ባለሙያዎች ጋር ልምድ ልውውጥ የተደረገበትና ሀገራዊ የድንገተኛ ህክምና ምላሽ ዝግጁነትን የሚያጠናክር ነው። ስልጠናው…
Read more

ጤና ሚኒስቴር በመላው ኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን እና የቀዝቃዛ ሰንሰለት ስርዓቶችን ለማጠናከር የፀሐይ ኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን እና ሞተር ሳይክሎችን ለክልል የጤና ቢሮዎች አስረክቧል።

በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ይህ ተነሳሽነት በጤና ተቋማት ውስጥ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሰፋ ተናግረዋል። 380 የጤና ተቋማት የፀሐይ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ያገኛሉ፤ ይህም ያልተቋረጡ አገልግሎቶችን ለማረጋገጥ ይረዳቸዋል ብለዋል። ሚኒስትሯ በተጨማሪም 1,183 በሃገር ውስጥ የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎች ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ክትባቶችን እና መድሃኒቶችን ለማድረስ እንደሚደግፉ አፅንኦት…
Read more