Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Month: September 2025

CERPHI

ከ15 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ሬዝደንት አማካሪዎች ቴክኖሎጂ በትምህርት ስርዓቱ ስለሚካተትበት ሁኔታ እየመከሩ ነው

ከ15 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ሬዝደንት አማካሪዎች በአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ችግሮችን በፍጥነት ለመለየት፣ ለመመርመርና ለማከም እንዲቻል ዘመን ያፈራው ቴክኖሎጂ በትምህርት ስርዓቱ በሚካተትበት ሁኔታ በአዲስ አበባ እየመከሩ ነው። የፊልድ ኢፒዲሞሎጅ ስልጠና ፕሮግራም ለህብረተሰብ ጤና አገልግሎት የጀርባ አጥንት መሆኑን የገለፁት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ቀጣዩ የአፍሪካ ጤና አገልግሎት በመረጃ ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ የኢፒዲሞሎጅ ባለሙያዎች…
Read more

የቻይና የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያየ

በዛሬው እለት ከቻይናው የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን (Chinese Disease Control and Prevention Authority /CDCPA/) የመጡ የልኡካን ቡድን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ሊሰሩባቸው በሚችሉ መስኮች ላይ መክረዋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እንግዶቹን በተቀበሉበት ወቅት ከዚህ ቀደም በሁለቱ ሀገራት ግንኙነቶች የተደረጉ የሰው ሀይል አቅም ግንባታና ስልጠና እንዲሁም የልምድ ልውውጥ ተግባራት አመርቂ ውጤቶች ማስገኘታቸውን…
Read more

12ኛው አመታዊ የ COECSA ኮንግረስ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

“የተርሸሪ የአይን እንክብካቤን በ COECSA ሃገራት ማሳደግ፡ ጊዜው አሁን ነው” በሚል መሪ ቃል 12ኛው የምስራቅ፣ መካከለኛ እና ደቡብ አፍሪካ የዓይን ህክምና ኮሌጅ (COECSA) ኮንግረስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። ኮንግረሱ አህጉራዊ እና አለምአቀፍ ባለሙያዎችን፣ የአይን ጤና ባለሙያዎችን እና ሰልጣኞችን ጨምሮ ከ40 በላይ ከሚሆኑ ሃገራት የተውጣጡ ከ600 በላይ ተሳታፊዎችን በማሰባሰብ በአፍሪካ የአይን ህክምናን ማሳደግ ላይ ምክክር ያደርጋል።…
Read more

የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ወር አፈጻጸም እና ሳምንታዊ የEOC ግምገማ ተካሄደ፤

ነሀሴ 15/2017 የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ወር አፈጻጸም እና ሳምንታዊ የEOC ግምገማ በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡ የአፈጻጸም ሪፖርቱ በልማት እቅድ ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ጽጌ የቀረበ ሲሆን ሳምንታዊ የEOC ሪፖርት በድንገተኛ በሽታዎች አሰሳ እና ቅኝት ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ነስረዲን ኑርዬ አማካኝነት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በግምገማ መድረክ የመምሪያው ኃላፊ ዶ/ር ሸምሱ…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ EOC ግምገማ አካሂዷል

በሳምንቱ ውስጥ የተከናወኑ የወባ ጫናን ጨምሮ ሌሎች 36 በሽታዎች ላይ ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ። የቢሮዉ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይ/ ዳይ/አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም የዚህን ሳምንት ቅኝት ሲያብራሩ በሳምንቱ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀምና የግንዛቤ ስራዎችን በማጠናክር የወባ በሽታ ከባለፈው ሳምንት አንፃር መቀነሱን ጠቁመዋል። እንደ አቶ ወልደሰንበት ገለፃ የወባ በሽታ…
Read more

የወቅቱ አየር ለወባ ወረርሽኝ ክስተት ምቹ በመሆኑ የወባ መከላከል ሥራ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ

የከምባታ ዞን የድንገተኛ አደጋዎችና ወረርሽኞች መከላከልና ቁጥጥር ግብረሀይል የወባ መከላከልና መቆጣጠር ስራን አስመልክቶ በየደረጃው እየተሠሩ ያሉ ተግባራትን የሚገመግም መድረክ በዱራሜ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩም የክረምት ወቅትን ተከትሎ ለወባ ትንኝ መራባት አመቺ የአየር ንብረት ሁኔታ በስፍት የሚታይ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን የወባ በሽታ ጫናን ለመግታት በወባ መከላከል፣ መቆጣጠር እና ማስወገድ ዙሪያ በዞኑ በሚገኙ መዋቅሮች እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት…
Read more

ትክክለኛ እና የተደራጀ የጤና መረጃ ስርዓትን በማጠናከር በህብረተሰቡ ላይ ሊክሰቱ የሚችሉ የጤና ስጋቶችን ቀድመን መከላከል እንደሚገባ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ከዞንና ከልዩ ወረዳ ለተውጣጡ የአደጋ ስጋት ግንኙነት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ተጠሪዎች (RCCE) ጋር የዉይይት መድረክ አካሂዷል ። በኢንስቲትዩቱ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ትክክለኛና የተደራጀ የጤና መረጃ ስርዓትን በማጠናክር በህብረተሰቡ ላይ ሊከሰቱ…
Read more

በበጀት አመቱ ኤች አይቪ ኤድስን የመከላከል እና መቆጣጠር ስራዎች በትኩረት መሰራታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ ፡፡

የቢሮው የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግመገማ እና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ አየተካሄደ ነው ፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃልፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ ባስተላለፉት መልዕክት በበጀት አመቱ ኤች አይቪ ኤድስን የመከላከል እና መቆጣጠር ስራዎች በትኩረት መሰራታቸውን አስረድተዋል። በበጀት ዓመቱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ EOC ግምገማ አካሂዷል

በክልሉ የወባ ጫናን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎች ላይ ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ። የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ ሳምንታዊ የአፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሳምንቱ 8242 የወባ ኬዝ ሪፖርት መደረጉንና ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ16 በመቶ መቀነሱን መመልከት ተችሏል። የቢሮው ጤናና ጤና ነክ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ከለላዉ አቻምየለህ የሳምንቱን ሪፖርት…
Read more

የጤና ሚኒስቴር፣ እና የክልል ጤና ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የጋራ የምክክር መድረክ በሐረር ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

መድረኩ የተሰሩ ስራዎች አፈጻፀም የሚገመገሙበት እና ተግዳሮቶችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑን የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ 2017 በጤና ዘርፍ አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡበት እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንድንጠነክር ያደረጉ እና ልምድ የተገኘባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 2017 የጤና ፖሊሲዎችን ለመተግበር የሚያስችል የጤና አዋጅ የጸደቀበት መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር መቅደስ፤ በቀጣዩ አመት የሪፎርም ትግበራ ላይ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡…
Read more